Get Mystery Box with random crypto!

ባህሩን በልከኛው አቀዛዘፉ አልፎ የጥበብን መንገድ የጠቆመ! በነጠረው ዒልሙ በሒክማው ነፀ | ረያን meme & islamic post


ባህሩን በልከኛው አቀዛዘፉ አልፎ የጥበብን መንገድ የጠቆመ!
በነጠረው ዒልሙ በሒክማው ነፀብራቅ አፅናፍን ያጥለቀለቀ!
የሰውነቱ መመንመን የበሽታው መፈራረቅ የአላህ ጠላቶችን ከመታገል ያላገዱት!
ከገበሬው እስከ ከተሜው ከመሀይሙ እስከ ሊቁ ሁሉንም በስብዕናው የገዛ!
ግዙፍ የዕውቀት ችቦ!
ተንቀሳቃሹ ቁርአን!
ገናናው ሰይድ ቁጡብ!

zinki

በግብፅ ሀገር ሞሻ በምትባል ከተማ በ1906 መካከለኛ ኑሮ ይኖሩ ከነበሩ ቤተሰቦች ተወለደ .....ገና በልጅነት እንድሜው እንደ ሌሎች ልጆች ተጫውቶ እና አፈር ፈጭቶ አላደገም ይልቁንስ ወደ መስጂድ መመላለስ ያዘውትር ነበር። የአስር አመት ልጅ ሲደርስም ከቁርአን ሁፋዞች ተርታ ተሰልፎ ነበር። የተዋጣለት ፀሐፊ እና እና ገጣሚ ነው። በብዕር ብልጭታው፣ በግጥሙ ውበት፣ በትርጉሙና በገላጭነቱ፣ በአነጋገር ዘይቤውና በአገላለፅ ዘዴዎቹ የሰውን ቀልብ በእጅጉ ማርኳል። ከአፉ የሚወረወሩት ንግግሮቹ ከመዳፉ የሚፈልቁት ፅሁፎቹ በግድ ጆሮህን ሰርስረው ወደ ልብህ ይዘልቃሉ።

"ንግግራችን በክብር የቆሙ ሙሽሮቻችን ናቸው በላኢላሀ ኢለላህ መንገድ እንጂ መንፈስም ሆነ ህይወት የለንም። ለላኢላሀ ኢለላህ ሲባል ሩህ በነፍሳችን ይርመሰመሳል። ሕይወትም በአካላችን ላይ ተነፍቷል" የሚለው ንግግሩ የበርካቶችን ልብ ንጧል።

በእምነት መፅናት አሸናፊነት ነው ይላል ብዙ ጊዜ
"የሙስሊሞች ድል ልክ እንደ ጉድጓዷ ሰዎች እንደ አስሐቡል ኡኽዱድ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ሰማዕት ሆነው የሚያሸንፉበት" ሲልም ይናገራል።

በዛሬው እለት ነበር እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ነሐሴ (August) 29/ በ1966 ዕለተ ሰኞ ረፋዱ ላይ በሚገ*ደል*በት ስፍራ ላይ ያቆሙት። ከመሞቱ በፊት አንድ ብጣሽ ወረቀት እና ብዕር ሰጥተውት እዚህ ወረቀት ላይ "አጥፍቻለው ይቅርታ" ብለህ ብቻ ፃፍ እና ከሞት ድነህ ነፃ እናውጣክ አሉት "ከአላህ ጋር በፈፀምኩት ግብይት ይቅርታን ከቶ ለመጠየቅ አልደፍርም" ሲል ዘመን ተሻጋሪና ታሪካዊ ንግግሩን ተናገረ

"‏لا اله الا الله منهج حياة"
“ላኢላሃ ኢለላህ የህይወት ጎዳና ነች” ስላለ ብቻ ገደ*ሉት። እሱን በመግ*ደል አስተሳሰቡን የቀጩ መልዕክቱንም ያደበዘዙ መስሏቸው ነበር። አዎ እሱን በመግ*ደል ያሸነፉ መስሏቸው ነበር! ግና እሱ ተሰዋና አሸነፈ እነሱም የሽንፈትን ፅዋ ተጎነጩ! አስተሳሰቦቹና መፅሃፍቶቹ በዓለም ላይ እንደ ወረርሽን ተሰራጩ። የገደ*ሉት መስሏቸው ሕያው አደረጉት።

أخي أنت حر وراء الصدود
أخي أنت حر بتلك القيود
إذا كنت بالله معتصما
فماذا يضيروك كيد العبيد

@Reyan_meme_and_islamic_post