2022-08-01 19:42:06
ከፍቅር ጓደኛችሁ አልያም ከትዳር አጋራችሁ ጋር ያላችሁ የፍቅር ግንኙነት በትክክለኛው መንገድ ላይ እየተጓዘ መሆኑን ማወቅ ነጋችሁን የተሻለ እና ስኬታማ እንዲሆን ያደርጋል። አሁን ያላችሁበት የፍቅር ግንኙነት በትክክለኛ መንገድ ላይ መሆኑን የምትፈትሹበት ጥያቄዎችን ይዘናል መልሱን ለናንተ
ከፍቅረኛችሁ ጋር ወይም ከትዳር አጋራችሁ ጋር አንድ ላይ በምትሆኑበት ወቅት በሆነ ጉዳይ በምትነጋገሩበት ጊዜ የመስማማትና ወደ አንድ የመምጣት ነገር ታያላቹ ወይስ ያለመስማማትና ልዩነት?
ከፍቅረኛቹ ወይም ከትዳር አጋራቹ በአካል ስትገናኙ ወይም በስልክ ስታወሩ የመሰላቸት ባህሪን ታያላቹ?
በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ያላችሁ አመለካከት ተመሳሳይ፣ተቀራራቢ ወይስ ሰፊ ነው?
የፍቅር አጋራቹን ምን ያክል አውቀዋለው ብላቹ ታስባላቹ?
ከፍቅር አጋራቹ ጋር ምን ያክል እርስ በእርስ ትተማመናላችሁ?
አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ወደ መለያየት ነው የሚወሰደው ወይስ ችግሩን ፈቶ የማስቀጠል ሁኔታ ነው ያለው?
የሆነ ነገር ስታደርጉ ከራሳችሁ እይታ ብቻ ነው የምታደርጉት ወይስ የፍቅረኛችሁን ስሜት ከግምት በማስገባት ከግል ውሳኔ ትጠበቃላችሁ?
የፍቅር አጋራችሁ ሁሉንም ነገር በሀላፊነትና በጥንቃቄ ነው የሚያደርገው ወይስ በግድ የለሽነት?
ከፍቅረኛቹ በላይ ቦታ የሚሰጠው ነገር አለን እንደ ቤተሰብ,ጓደኛ ወይም ሌላ?
የፍቅር አጋራችሁ ላይ በተደጋጋሚ ውሸትና ምክንያት የሚበዛ ነገርን ትመለከታላችሁ?
ለመልዕክት @RMG_DM ይጠቀሙ።
SHARE SHARE
@Relationship_and_Marriage_Goal
@Relationship_and_Marriage_Goal
2.1K viewsedited 16:42