Get Mystery Box with random crypto!

Abu Hanif Redwan Mohammed

የቴሌግራም ቻናል አርማ redwan_rm — Abu Hanif Redwan Mohammed A
የቴሌግራም ቻናል አርማ redwan_rm — Abu Hanif Redwan Mohammed
የሰርጥ አድራሻ: @redwan_rm
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 272
የሰርጥ መግለጫ

الحق أحق أن يتبع ولو خالف هواك وجفاك أصدقاؤك!
ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/redwan.mohammed.37454961
.
https://m.facebook.com/redwan.rm.50
ቴሌግራም: https://t.me/redwan_RM
ትዊተር: https://twitter.com/Abu_Hanif_RM
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/abu_hanif_rm

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 13:54:07 የተክቢርን ሱና ህያው አድርጉ!
=====================

[ الله أكبر الله أكبر الله أكبر، لا إله إلا الله، والله أكبر الله أكبر، ولله الحمد ]

" አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ "
----------------
13 views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 13:53:45 የዒድ ተክቢራ!
----------
@redwan_RM
14 views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:10:50
የዐረፋ ( ከዙል–ሒጃህ 9ኛው) ቀን ፆም!
-----------------
ነቢዩ–ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም– ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው፦ [ ያለፈውን አመት እና ቀጣዩን አመት ወንጀል ያሰርዛል] ብለዋል።

ስለዚህ ነገ ጁምዓ የዐረፋ ቀን ነውና በፆም፣ በዱዓ እንበርታ!
በአግባቡ ፆመው ወንጀላቸው ከሚሰረዝላቸው ያድርገን!
29 viewsedited  12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:00:35 የአረፋ ቀን ፆም!

ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

‎﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።

ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።

ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።

በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት

ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም። ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ አርብ ሐምሌ 1 ነው።ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ። ለራሳችን፣ለቤተሰባችንና ለሀገራችን ዱዓ እናድርግ።
30 views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 16:49:20
جدول مقترح لختم القرآن في عشر ذي الحجة
الدال على الخير كفاعله
استفيدوا منه وانشروه في مواقع التواصل
https://t.me/badratkhaier
71 views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:07:17
عاجل:
أعلنت #المحكمة_العليا بـ #السعودية أن:
01 #ذي_الحجة: الخميس 30 يونيو.
#يوم_عرفة (09 ذو الحجة): الجمعة 08 يوليو .
#عيد_الأضحى (10 ذو الحجة): السبت 09 يوليو.
https://t.me/badratkhaier
#مشروع_بذرة_خير_الدعوي
#هلال_ذو_الحجة
51 views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 15:01:40 ما من أيام أفضل عند الله ولا العمل فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر، فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير وذكر الله، وإن صيام يوم منها يعدل بصيام سنة، والعمل فيهن يضاعف سبعمائة ضعف

“በደረጃቸውም ሆነ በውስጣቸው በሚሠራ ሥራ ከነኚህ አሥር ቀናት የሚበልጥ በአላህ ዘንድ አንድም የለም። በነሱ ውስጥ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር ማለትንና አላህን ማውሣት አብዙ። ከነሱ ውስጥ አንድ ቀን መፆም የአመት ፆምን ይስተካከላል። በነሱ ውስጥ የሚሠራ ሥራ እስከ ሰባት መቶ ድረስ እጥፍ ድርብ ይሆናል።” (በይሀቂና ኢማም አህመድ ዘግበውታል)

4. በነሱ ውስጥ ተክቢራ ማብዛት

ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እና አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) በአሥርቱ ቀናት ውስጥ “አላሁ አክበር!” እያሉ ወደ ገበያ ይወጣሉ። ሰዎችም የነሱን ተክቢራ እየተቀበሉ “አላሁ አክበር!” ይሉ ነበር። እንዲህም ብለዋል። “ዑመር በሚና በሚገኘው ቁባቸው ውስጥ ተክቢራ ያደርጉ የነበረ ሲሆን በመስጅድ ውስጥ ያሉ ሰዎችም እርሣቸውን ይሰሙና ‘አላሁ አክበር!’ ይሉ ነበር። ገበያ ውስጥ ያሉ ሰዎችም ሚና በተክቢራ እስክትናወጥ ድረስ ‘አሏሁ አክበር!’ ይሉ ነበር።” ብለዋል። (ፈትሁል ገፋር ቀጽ 5፣ ገጽ 379)

5. ሀጅ ሥራ ውስጥ ላልተሠማራ ሰው የመጀመሪያዎቹን ዘጠኝ ቀናት መፆም

ይህንንም ሀሠን፣ ኢብኑ ሲሪን እና ቀታዳህን የመሣሰሉ ታቢዒዮችን ጨምሮ በርካታ ሰሃቦች ሰርተውታል። ኢማም ነወዊ እንዲህ ብለዋል፡-

ليس في صوم هذه التسعة كراهة بل هي مستحبة استحبابًا شديدًا، لا سيما التاسع منها، وهو يوم عرفة

“አነኚህ ዘጠኝ ቀናት መፆማቸው የሚጠላ አይደለም። ባይሆን እጅግ ተወዳጅ ነገር ነው። በተለይም ዘጠነኛው ቀን። እሱም የዐረፋ ቀን ነው።” (ሸርሁል ሙስሊም ቀጽ 3፣ ገጽ 245)

ከአቢ ቀታዳህ እንደተዘገበው ደግሞ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ። እንዲህም አሉ፡-

يكفِّر السنة الماضية والباقية

“ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል።” (ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል)

6. ቁርዓንን ማንበብ

ከኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

من قرأ حرفًا من كتاب الله فله به حسنة، والحسنة بعشر أمثالها، لا أقول الم حرف، ولكن ألف حرف، ولام حرف، وميم حرف

“ከአላህ ኪታብ አንድ ፊደል ያነበበ ሰው የመልካም ምንዳ አለው። አንዱ መልካም ምንዳ አሥር ተመሣሣይ እጥፍ ይባዛል። አንድ ሰው ‘አሊፍ-ላም-ሚም’ ያለ እንደሆነ አንድ ፊደል አይደለም። ነገርግን ‘አሊፍ’ አንድ ፊደል ነው፣ ‘ላምም’ አንድ ፊደል ነው፣ ‘ሚምም’ አንድ ፊደል ነው።” (ቡኻሪና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

7. ኡድሂያ ማዘጋጀት

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ [١٠٨:٢]

“ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ (በስሙ) ሰዋም።” (አል-ከውሰር 108፤ 3)

ከዓኢሻ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما عمل آدمي من عمل يوم النحر أحب إلى الله من إهراق الدم، وإنها لتأتي يوم القيامة بقرونها وأشعارها وأظلافها، وإن الدم ليقع من الله بمكان قبل أن يقع على الأرض فطيبوا بها نفسًا

“ከነህር /እርድ/ ቀን ሥራዎች ውስጥ የአደም ልጅ ደምን ከማፍሠስ በላይ ወደ አላህ ተወዳጅ የሆነ አንድም ሥራ አልሠራም። እርዷም የቂያማ ቀን ከነፀጉሯና ጥፍሯ ትመጣለች። ደሙም መሬት ላይ ከማረፉ በፊት ከአላህ ዘንድ ቦታ ይይዛል። በዚህም ነፍሣችሁን አስደስቱ (ደስ ይባላችሁ)።” (ቱርሙዚ፣ ሃኪም እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል)

ኡድሂያ ማረድ የተዘጋጀ ሰው ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን የሰውነቱን መንካት የለበትም። ከኡሙ ሰለማ (ረ.ዓ) በተላለፈው ሀዲስም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡-

إِذَا دَخَلَتِ الْعَشْرُ وَأَرَادَ أَحَدُكُمْ أَنْ يُضَحِّيَ فَلا يَمَسَّ مِنْ شَعَرِهِ وَبَشَرِهِ شَيْئًا

“አንዳችሁ ኡድሂያ ለማረድ አስቦ አሥርቱ ቀናት የገቡ እንደሆነ ከፀጉሩም ሆነ ከሰውነቱ አንዳቸም ነገር አይንካ።” ብለዋል። (ሙስሊም እና ነሣኢ ዘግበውታል።)

አላህ እነዚህን ውድ ቀናቶች ከሚጠቀሙት ያድርገን።»

منقول
90 views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 15:01:26 «አሥሩ የዚልሂጃ ቀናት- ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮች

ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ እጅግ በላጮች የሆኑት የመጀመሪያዎቹ አሥሩ የዚልሂጃ ወር ቀናት ናቸው። እነሆ እነኚህ ምርጥ ቀናት ከፊት ለፊታችን ተደቅነዋል። ለዚህም ይመስላል ሙስሊሙ የአላህን ቤት ከዕባን ለመጎብኘት ያለው ጉጉቱ ድንበር አልፏል፤ በከዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ፣ በሶፋና መርዋ መካከል ለመሮጥ እና ዐረፋ ላይ ቆሞ አላህን ለመለመን ያለው ስሜት ጣሪያ ነክቷል። የታላቁን ነቢይ መስጅድ መስጅደ-ነበዊን ለመጎብኘትና በመስጅዱ ውስጥ በተከበረው ቦታ ረውደቱ ሸሪፋ ላይ ለመስገድ ያለው መነሣሣት ውስጥን ይነቀንቃል፤ በሀሣብ ያምሣል፣ ክንፍ ቢኖር “ምነዋ ወደዚያ ወደተቀደሰው ምድር በበረርኩ!” ያስብላል።

ወዳጆቼ! እኛስ እነኚህ እጅግ የተባረኩና የተከበሩ ቀናቶች ከያዙት ምንዳ ለመቋደስ ምን ማድረግ እንችል ይሆን?

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘወትር በትእዛዙ በመገኘት ለቋሚው ሀገራቸው ለሚሰንቁ መልካም ባሮቹ በነኚህ በተባረኩ ቀናት ውስጥ ምን ዓይነት ትልቅ ምንዳ ይሆን ያዘጋጀላቸው?

የዚልሂጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ታላቅነት

1. አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የማለባቸው ቀናት መሆናቸው

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَالْفَجْرِ ﴿١﴾ وَلَيَالٍ عَشْرٍ ﴿٢﴾ وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ ﴿٣﴾

“በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም። በጥንዱም በነጠላውም።” (አል-ፈጅር 89፤ 1-3)

ከጃቢር ኢብኑ ዐብዱላህ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እነኚህ አሥር ቀናቶች የትኞቹ እንደሆኑ በሚያመላክተው ሀዲሣቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-

العشر عشر الأضحى، والوتر يوم عرفة، والشفع يوم النحر

“አሥሩ ማለት አሥሩ የአድሃ ቀናት ናቸው። ‘ወትር’ /ጥንዱ/ የተባለው የዐረፋ ቀን ሲሆን ‘ሸፍዕ’ /ነጠላው/ ማለት ደግሞ የነህር /የእርዱ/ ቀናት ናቸው።” ብለዋል። ሀዲሱን ኢማም ነሣኢ እና ሃኪም በሙስሊም መስፈርት መሠረት ሰሂህ ትክከለኛ ሀዲስ ነው ብለውታል።

ኢማም በይሀቂ ከዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር እንደዘገቡት ደግሞ:-

ليالٍ عشر، العشر الثماني، وعرفة، والنحر

“አሥርቱ ሌሊቶች የመጀመሪያዎቹ ስምንቶቹ፣ የዐረፋ ቀን እና የእርድ ቀን ናቸው።” ብለዋል።

2. እነኚህ ቀናት “አያም መዕሉማት” /የታወቁ ቀናት/ም ይባላሉ

ይህም በሚከተለው የቁርዓን አንቀፅ ውስጥ የተጠቀሠ ነው።

وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ [٢٢:٢٨]

“በታወቁ ቀኖችም ውስጥ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ” (አል-ሀጅ 22፤ 27)

“የቁርዓን ተርጓሚ” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ሰሃባ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ እነኚህ ቀናት “አሥርቱ ቀናት” ናቸው ያሉ ሲሆን በነኚህ ቀናት ውስጥ ታላቁን ጌታ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን በብዛት ማውሳት የተወደደ ነው።

3. ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮቹ

ይህም በሚከተለው ሀዲስ ውስጥ ተነግሯል። ከጃቢር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

أفضل أيام الدنيا أيام العشر، يعني: عشر ذي الحجة، قيل: ولا مثلهن في سبيل الله؟، قال ولا مثلهن في سبيل الله إلا رجل عفر وجهه في التراب، وذُكر عرفة، فقال يوم مباهاة ينزل الله تبارك وتعالى إلى سماء الدنيا، فيقول: عبادي شعثًا غبرًا ضاحين، جاءوا من كل فجٍّ عميق يسألون رحمتي، ويستعيذون من عذابي ولم يروا، فلم نر يومًا أكثر عتيقًا وعتيقة من النار

“ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮቹ አስሩ ቀናት ናቸው። ማለትም አሥሩ የዚልሂጃ ቀናት። በአላህ መንገድ ላይ መውጣትም ቢሆን የነሱ አምሣያ የለምን? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ‘በአላህ መንገድ ላይም ቢሆንም እነሱን የሚመስል የለም። ፊቱ ከአፈር የተገናኘ ሰው (በአላህ መንገድ ላይ የሞተ) ሲቀር።’ አሉ። ስለ ዐረፋም ተወሳና መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ‘እሱ የሙባሃት /አላህ በባሮቹ የሚኩራራበት/ ቀን ነው። አላህ ወደ ቅርቢቱ ዓለም ይወርድና ባሮቼ ተንጨፋረው፣ አቧራ የለበሱ ሆነውና ተጎሣቁለው እሩቅ ከሆነ አቅጣጫ ሁሉ እዝነቴን ሊጠይቁ እሷን ያላዩ ሲሆን ከእሣቴም በኔ ሊጠበቁ መጡ። ወንድም ሆነ ሴት በብዛት ከእሣት ነፃ የሚወጡበት እንዲዚህ ቀን አላየንም’።” (በዛር ሀዲሱን ዘግበውታል)

4. በርካታ የሀጅ ሥራዎች የሚሠሩት በነኚህ ቀናት ውስጥ ነው

ከነኚህም መካከል የዚልሂጃ ስምንተኛ ቀን በሙዝደሊፋ ይታደራል፤ በዘጠነኛው ቀን በዐረፋ ላይ ይቆማል፤ ከዚህም በተጨማሪ ለመስዋእት የሚሆን እንሠሳት መንዳት፣ ጠጠር መወርወር፣ ፀጉር መላጨት አሊያም ማሣጠር፣ በዚልሂጃ አሥረኛው ቀን ጠዋፍ ማድረግንና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

5. የአምልኮ ዘርፍ የሆኑት ዋና ዋናዎቹ የሚሰበሰቡባቸው ቀናቶች ናቸው

ኢማም ሃፍዝ ኢብኑ ሀጀር ፈትሁልባሪ በተሠኘው ታዋቂ ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ይላሉ

والذي يظهر أن السبب في امتياز عشر ذي الحجة لمكان اجتماع أمهات العبادة فيه، وهي الصلاة والصيام والصدقة والحج، ولا يتأتى ذلك في غيره

“የዚልሂጃ አሥርቱ ቀናትን ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ቦታው ከአምልኮ ተግባራት ዋና ዋና የሚባሉት በአንድ ላይ ተሰባስበው የሚሠሩበት መሆኑ ነው። ይሀውም ሰላትን፣ ፆምን፣ ሰደቃን (ምጽዋትን) እና ሀጅን ያጠቃልላል። ከነኚህ ቀናት ውጭ እነኚህ ሁሉ ነገሮች አንድ ላይ የሚሰባሰቡበትን አጋጣሚ አናገኝም።” (ፈትሁልባሪ ቅጽ 2፣ ገጽ 462)

በነኚህ ቀናት ውስጥ ከሚወደዱ ሥራዎች መካከል

1. ሐጅና ዑምራ ማድረግ

በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ ምርጥ የአምልኮ ሥራዎች ናቸው። ምክኒያቱም የነኚህ አምልኮ ሥራዎች ትክክለኛ ወቅቱ ይህ ነውና። ከአቢሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ አሉ:-

العمرة إلى العمرة كفارة لما بينهما، والحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة

“አንደኛው ዑምራ እስከ ሌላኛው ዑምራ በመካከላቸው የተሰራ ወንጀልን ያብሣል፤ መብሩር /የተሟላ/ የሆነ ሀጅ ምንዳው ጀነት ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2. በበጎ ሥራዎች ላይ መበርታት

ከዐብዱላህ ኢበብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما مِن عمل أفضل من عمل فى هذه الأيام العشر، قالوا: ولا الجهاد؟ قال ولا الجهاد إلا رجل خرج بماله ونفسه فلم يرجع منه بشيء

“በነኚህ አሥር ቀናት ውስጥ የሚሠራ ሥራን የሚበልጥ ምንም የለም። ‘ጅሃድም ቢሆን?’ አሏቸው። እርሣቸውም ‘አዎን ጅሃድም ቢሆን ገንዘቡንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ያልተመለሰ ሰው ብቻ ሲቀር።’ አሉ።” (ኢማም አህመድና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

እንዲሁ በሌላ ዘገባም:-

لا تطفئوا سرجكم ليالي العشر

“በአሥርቱ ቀናት ለሊቶች ውስጥ መብራታችሁን አታጥፉ።” የሚል ዘገባ የመጣ ሲሆን ይህም ትርጉሙ “በነኚህ ቀናት ውስጥ ቁርዓን ቅሩ፣ በሰላትም በርትታችሁ ቁሙ ለማለት ነው” ተብሏል።

3. ዚክር ማብዛት

ከኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:-
66 views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 22:53:03 በልጆች ላይ ያንዣበበ ከባድ አደጋ!

ያለንበት ዘመን ልጆች በእጃቸው ላይ ባሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሌት ተቀን በሚያዩዋቸው የቴሌቪዥን ቻናሎች፣ በግልፅና ስውር መርዛቸውን በሚያሰራጩ ካርቶን ፊልሞች ምክንያት ስነምግባራቸው፣ እምነታቸው በአደገኛ ሁኔታ ተጽእኖ ላይ እየወደቀ ያለበት ነው።

ታዲያ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ማነው?

በፍፁም ታማኝነትና በሐቀኝነት ወደ ራሳችን መመለስ ይገባናል! ይህን ጥያቄ ሁላችንም ራሳችንን መጠየቅ ግድ ይለናል!

ተጠያቂው እኔ! አንተ! አንቺ! እኛ ሁላችንም! ካልሆን ማን ሊሆን ነው???

ባለንበት ተጨባጭ ነገራቶች በፍጥነት እየተለዋወጡ፣ ብልሹነትና ጥፋት እንደ ሰደድ እሳት ከአፅናፍ አፅናፍ እየተስፋፋ ፤ ሸይጣንና ጋሻ ጃግሬዎቹ የአላህ አደራ የሆኑ ልጆቻችንን የጥፋት ማጥ ውስጥ ለመጨመር ባለ በሌለ ኃይላቸው እየተጋጋጡ የሚገኙበት ነው። ይህንን አደጋ ልብ ብለን ልናስተውል፤ ዓይናችንን ከፈት አድርገን ልንመለከት ይገባል።

ሁላችንም ኃላፊነታችንን ለመወጣት ጥረት ልናደርግ ይገባል። እኛ ግዴታችንን መወጣት ካልቻልን ግን ዓይናችን እያየ የሰውና የጂን ሸይጣናት ልጆቻችንን ከእጃችን ይነጥቁናል። ለሚፈልጉት የጥፋት አላማ ይመለምሉልናል።

አላህ ልጆቻችንን ይጠብቅልን!

I ሂዳያ ተርቢያ I #ተግሳፅ I

https://t.me/HidayaTerbiya
111 views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 13:41:41
#ሳዑዲ_አረቢያ

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሪያድ የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን እቃዎች ከሱቆች እና ከመደብሮች እየሰብሰበ ይገኛል።

የሳዑዲ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃል በሚል የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን አሸንጉሊቶች፣ ቲሸርቶች፣ የጸጉር ማስያዣዎች፣ ኮፊያ፣ እና የእርሳስ መያዣወችን ከየመደብሩ እንዲሰበሰቡ እያደረገ ነው።

የሀገሪቱ መንግስት ህፃናትን ለመጠበቅ ሲል " መርዛማ መልዕክት " የያዙ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚያስተዋውቁ ቀለም ያላቸውን እቃዎችን ከሱቅ እና ከመደብር እየሰበሰበ መሆኑን ገልጿል።

አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እቃዎቹ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነውን ማህበረሰብ ሞራልና እሴት የሚጻረሩ እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለተመሳሳይ የፆታ ግንኙነት የሚያበረታቱ ናቸው ብለዋል።

የሳዑዲ ንግድ ሚኒሰቴር በትዊተር ገፁ ፤ እቃዎቹን የመሰብሰብ ዋና ትኩረት " ለሳውዲ ህዝብ እሴቶች የማይመጥን ቀለም ያላቸው እቃዎች " ማስወገድ ነው ብሏል። ሚስቴሩ ተመሳሳይ እቃዎች ሲሸጡ በሚገኙ ሱቆች ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ከዚህ ባለፈ ሳዑዲ አረቢያ በቅርቡ ሁለት የዲስኒ እና ማርቭል ፊልሞችን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃሉ በሚል አግዳለች።

በሳዑዲ አረቢያ ምድር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ህገወጥ ሲሆን #እስከሞት ድረስ ያስቀጣል።

ቪድዮ - DW

@tikvahethiopia
160 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ