Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነት ከኢትዮጲያዊ ወጎች ጋር

የቴሌግራም ቻናል አርማ realhabeshawi — ኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነት ከኢትዮጲያዊ ወጎች ጋር
የቴሌግራም ቻናል አርማ realhabeshawi — ኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነት ከኢትዮጲያዊ ወጎች ጋር
የሰርጥ አድራሻ: @realhabeshawi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 438
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ሐገራችን ታሪክ ማንነት እና የአባቶቻችንን አርበኝነት አንዘክራለን
በኩራት ኢትዮጲያዊነትን ከጫፍ እሰከ ጫፍ እናስተጋባለን
ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት @enkyopaz
💚💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️❤️
የከፍታሽ ልኬት ቅድስና ሲሆን ውቢቷ ሀገሬ
ትንሳኤሽ ቅርብ ነው ህዝብሽ ያወድሳል በልልታ ዝማሬ
💚💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️❤️

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-21 23:28:49
ናዕት
ናዕት: [ነገር ስም] ሳይቦካ ተለውሶ በቂጣነት የሚጋገር ማለት ሲሆን እስራኤላውያን በግብፅ ሳሉ በሚያዝያ ወር የፋሲካ በዐልን በቂጣ እንጀራ ስላከበሩ በዐለ ናዕት ተባለ።

የኔ ሙሉ ሰው ቴዶዬ
129 views˙·٠•● Real habeshawi ●•٠·˙, edited  20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 23:27:33 ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከደቂቃዎች በፊት የለቀቀውን 'ናዕት' የተሰኘውን ሃገራዊ ዜማ

"መታሰቢያነቱ ላለፉት አራት አመታት በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች አላግባብ በግፍ ለተገደሉ ፣ አካላቸው ለጎደለ እና ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ንፁሃን ዜጎች በሙሉ ይሁን"ሲል ገልፆል


#ናዕት
Teddy Afro
125 views˙·٠•● Real habeshawi ●•٠·˙, 20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 23:27:02 ሙሉ ግጥም

ናዕት

ዶፍ ዶፍ...
ግርም እያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ
ኡኡ ሬጌ ናዕት
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ማን ሊታደም ከድግሱ
ብልጭልጭ ቢሆን ድንኳን
አይለውጥ ጎግ የእውነት መልኳን
ቢጋርድ ሀሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌ ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው
ዘውግ ያወረው ድንበር መኃላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አዕላፍ እሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደሞ በነ ኡኡ ሬጌ
ኡኡ...ሬጌ ናዕት...
ኡኡ ሬጌ ናዕት
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ማን ሊታደም ከድግሱ...?
ተላላ ዝንጉ ሰብ የሙታን ሸማ ደዋሪ
ምን አለ አይል ከፊት ሆኖ ቅርብ አዳሪ
ተናገር አፌ ደፍረህ ሳትናወጥ ከቶ
ዝም አይሆንም ሜዳ ተራራ ሞት መጥቶ
ከበሮ ግም ሲል በእምቢ ነጎድጓድ ምቱ
ይናዳል የዘር ድንዛዜ ያ ድውዬ ቤቱ
ገለሌ በል ኤሳው ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት
ብታገስ ባሰ ባንተ የልቤ እሳት
እያመመው መጣ እያመመው
ያዳፈነው እሳት ከሆዱ ሳይወጣ
ልቤ እንደካቻምናው እያመመው መጣ
የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ... እያለ ማሲንቆ
ኡ...ኡ...
እያመመው መጣ
የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባ ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት
እያመመው መጣ...
ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሐገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም
ዶፍ ዶፍ
ዶፍ ቢዘንብ እሳት ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዶፍ
ዳር አለው እንዴ ድንበር
ዳር አለው እንዴ ፍቅር
የዘር ሀይማኖት ድንበር
ዳር አለው እንዴ ፍቅር
በዚህ ለጸና እውነት
የፍቅር ሀገር ከጥንት
ዘብ ያድራል ሁሉም እስከ ሞት
ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት
ዶፍ ዶፍ
ዶፍ ቢዘንብ እሳት ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
189 views˙·٠•● Real habeshawi ●•٠·˙, 20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 10:03:22 እንኳን ለሚያዚያ 27 ፤ የአርበኞች የድል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!! 

የኢትዮጵያ አርበኞች፤ ለሃገር ነጻነት፣ አንድነትና ክብር፤ የኢጣልያ ፋሽስት ወራሪ ሃይልን በመመከት፤ ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን ያስጨነቀበት እና ድል ያደረገበት አልበገር ባይነትን ያስመሰከሩበት ቀን ነዉ፡፡

#Join now
# share


246 views˙·٠•● Real habeshawi ●•٠·˙, edited  07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 02:17:01
304 views˙·٠•● Real habeshawi ●•٠·˙, 23:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 02:17:01
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሠላም፤
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሠላም።


#እንኳን_አደረሳችሁ
#ኢትዮጲያ_ትንሳኤሽን_ያሳየን
262 views˙·٠•● Real habeshawi ●•٠·˙, 23:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 00:52:56 Channel photo updated
21:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 23:49:03 ነፃነት ዋጋዉ ስንት ነዉ? ? ?
439 viewsEEF, 20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 23:45:13
ነፃነት ዋጋዉ ስንት ነዉ????


እባክዎ ያድምጡት
420 viewsEEF, 20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ