Get Mystery Box with random crypto!

እስከ መጨረሻው ያንብቡት! በአንድ አካባቢ 'እብድ' ተብሎ በማህበረሰቡ የሚጠራ ሰው ነው። ይህ ሰ | Happy_life®

እስከ መጨረሻው ያንብቡት!

በአንድ አካባቢ 'እብድ' ተብሎ በማህበረሰቡ የሚጠራ ሰው ነው። ይህ ሰው ወደ ባንክ ጎራ ይላል። የያዘውን የባንክ ደብተርም ለአንድ የባንኩ ገንዘብ ከፋይ ይሰጥና “5,000 ብር ማውጣት እፈልጋለሁ” ይለዋል፡፡

የባንኩ ሰራተኛም እብዱን ሰው “ከ 10,000 ብር በታች የሆነ ገንዘብ ለማውጣት እባክዎን ኤቲኤም ይጠቀሙ” ይለዋል ፡፡
እብድ ሰውየውም “ለምን?” ሲል ጠየቀ ፡፡ ገንዘብ ከፋዩም በቁጣ “ይህ የባንካችን ህግ ነው፡፡ ሌላ ጉዳይ ከሌለህ እባክህ ውጣ። ከኋላህ ወረፋ የሚጠብቁ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡ ” ብሎ ደብተሩን ለእብዱ ሰው መለሰ፡፡

እብዱ ሰውም ዝም አለ ፡፡ ግን የባንክ ደብተሩን ለገንዘብ ከፋዩ መለሰና “እባክህ በአካውንቴ ውስጥ ያለኝን ገንዘብ በሙሉ እንድወስድ እርዳኝ” አለው፡፡

በዚህ ወቅት ገንዘብ ከፋዩ የአካውንት ቁጥሩን በማንበብ የእብዱን ሰው ቀሪ ሂሳብ ሲፈትሽ እጅግ ተገረመ ፡፡ ጭንቅላቱን ነቀነቀና ተንበረከከ እና እብድ ለሆነው ሰው።

“ይቅርታ አድርጉልኝ ጌታዬ በሂሳብዎ ውስጥ 3.5 ቢሊዮን ብር አለዎት እናም ባንኩ በአሁኑ ወቅት ያን ያህል ገንዘብ የለውም። ቀጠሮ መያዝ እና ነገ እንደገና መምጣት ይችላሉ?

እብድ ሰውየውም “አሁን ምን ያህል ማውጣት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀ።

ገንዘብ ከፋዩም “ማንኛውም መጠን እስከ 300,000 ብር ድረስ” አለው።

ይህ እብደ ሰው ከዛም 300,000 ሂሳቡን ከራሱ ሂሳብ ማውጣት እንደሚፈልግ ለገንዘብ ከፋዩ ነገረው።
ከፋዩም በፍጥነት ይህን አደረገ እናም ለእብዱ ሰው በአክብሮት ሰጠው።

እብዱ ሰው 5,000 በቦርሳው ውስጥ አስቀመጠና የባንኩን ሰራተኛ የ295, 000 ቀሪ ሂሳብ እንዲያስገባለት ጠየቀ ፡፡
ገንዘብ ከፋዩም ደነዘዘ።

ህጎች ተለዋዋጭ (flexible) አይደሉም እኛ ሰዎች ግን ሁኔታዎች እንድንሆን ሲያስፈልጉ ተለዋዋጭ (flexible) መሆን እንችላለን።

ሰዎችን በመልካቸው ወይም በአለባበሳቸው ላይ ተመስርተን ማስተናገድ የለብንም!
ይልቁንም ማንኛውንም ሰው በአክብሮት ልንይዘው ይገባል፡፡
መጽሐፍን በሽፋኑ ለመገምገም በጭራሽ አይቸኩሉ!
ቸር ንባብ
መልካም ምሽት !!
ሁሉም ሰው አስፈላጊ ነው!
አስተማሪ ሆኖ ካገኙት share ያድርጉት