Get Mystery Box with random crypto!

ባሏን የገደለው 'መርዝ' =============== ከለታት አንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ | Happy_life®

ባሏን የገደለው 'መርዝ'
===============
ከለታት አንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በ ሁለተኛው
ዓመት ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።
ይህች ቆንጆ ልጅት አንድ ቀን ጠዋት ወደ እናቷ ቤት ብርር ብላ በመሄድ፦
"እማዬ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው የማይረባ ነገሮች
ሰልችተውኛል ለኔ አያስብልኝም ዞር ብሎ አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል ፈልጋለው በሌላ በኩል ህግ ያስረኛል ብዬ እፈራለው እባክሽ እርጂን " አለቻት።
እናቷም "እሺ ውድ ልጄ እረዳሻለው ነገር ግን አንዳንድ የምታደርጊያቸውነገሮች አሉ"። አለቻት።
ልጅቷም " አንቺ ያልሽኝን ሁሉ አደርጋለው አለች"
እናትየውም "ባልሽ ሞቶ ሬሳው ከቤትሽ እስከሚወጣ ድረስ ከዛሬ ጀምሮ የምታደርገውን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሚው አለች፦
1. የገደለችው እሷናት ብለው ጎረቤት እንዳይጠረጥሩሽ ከአሁን ሰዓት
ጀምረሽ ከባልሽ ጋር ሰላም ፍጠሪ
2. ሁልግዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ቆንጆ ሆነሽ ታይ
3. በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኚለት አበረታችው
4. ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ ብዙ ግዜ አዳማጭ ሁኝ በማክበር
ታዘዥው
5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ ለእሱ ጥቅም ብቻ አድርጊው እንዲች ብለሽ
ለራስሽ እንዳትጠቀሚ ገንዘብ ከከለከለሽ አትናገሪ ዝም በይ
6. ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳይጠረጥርሽ የጭቅጭቅና የጩኸት
ድምፅ አታሰሚ ሰላምና ፍቅር ብቻ ከአፍሽ ይውጣ ... እስከ ምትገላገይውድረስ ብቻ ነው።
እናትዮዋ፦ በድጋሚ "ሳታዛንፊ ያልኩሽ ታደርጊያለሽ?" አለቻት።
ልጅቷም " እሱ ብቻ ሞቶ ሬሳው ይውጣልኝ እንጂ አደርገዋለሁ" አለች።
እናትየዋም የሆነ ብልቃጥ እየሰጠቻት፦ " ይህንን መርዝ ያዥው ቀስ እያለ ውስጡን አመንምኖ እንዲገድለው በየቀኑ ምግቡ ውስጥ ጠብ እያደረግሽስጭው" አለች።
ልጅቷም ድስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።
ከአንድ ወር ብሓላ ልጅቷ ወደ እናቷ ቤት ተመልሳ መጣች። እንዲህ
አለቻት" ወይ ጉድ ሰውዬው ወሬ ሰምቶ ይሁን ወይ ቀልቡ ነግሮት? ድሮ
ዞር ብሎ የማያየኝ ሰውዬ ፣ ፍቅሬ፣ማሬ ፣ወለላዬ፣ ህይወቴ፣ ንግስቴ፣ በዓለም ላይ የምታክልሽ ሴት የለችም ይለኝ ጀምሯል ብቻ እኔንጃ ጸባዩ ልውጥ አለብኝ"
እናትየውም፦ መርዙን እየሰጠሽው ነው? አለቻት
ልጅቷም አይኗ ላይ እንባ እየቀረረ ፦ አዎ ግን አሁን ጸባየ ሸጋ ጣፋጭ አፍቃሪ ባል ሆኗል እንዲሞትብኝ አልፈልግም ማርከሻ ሌላ መድሃኒት ካለፈልጊልኝ እባክሽ ጸጸቱ ሊገለኝ ነው።
እናትየዋ፦ ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ጸባየ መጥፎውን ባልሽን የገደልሽው "መርዟአንቺ ነሽ" ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣ መታዘዝ፣ መንከባከብ፣ መታገስ፣ማክበር እና ውብ ሆነሽ ስትገኚ ባልሽን መለወጥ ችለሻል። አንቺ ለሌላውሰው ምንም ነገር ሳትሰጭ እንዴት ከሌላ ሰው ያልሰጠሽውንትጠቢቂያለሽ? ፍቅር ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው። ቅድሚያ ግን መስጠትያስፈልጋል ፍቅር ከሰጠሽው ፍቅር ታገኝያለሽ ጸብና ጭቅጭቅ ይዘሽየምጠብቂው ከሆነ ያንኑ ታገኛለሽ።ምላሽ ሳትጠብቂ ከራስሽ አስበልጠሽ በሁሉም ነገር ባልሽን አስቀድሚ
ፍቅር ስጭው!!!
ምንጭ ከወሬ ፏፏቴ

ለናንተለቆንጃጂት እህቶቼ ይሁንልኝ በያላችሁበት መልካም ቀን ፍቅርና ሠላም ለውዷ አገራችን ኢትዮጵያ !!!