Get Mystery Box with random crypto!

ለስንፍና ምክንያት ስተሰጥ እና ለሌላ አጀንዳ በር ለመክፈት ሲፈለግ ደም የሰጠውን መሪ፣ ደም በመስ | የብልፅግና ወዳጅ/Prosperity Lover

ለስንፍና ምክንያት ስተሰጥ እና ለሌላ አጀንዳ በር ለመክፈት ሲፈለግ ደም የሰጠውን መሪ፣ ደም በመስጠት እና አርአያ ሆኖ ሀገር የሚመራውን መሪ መውቀስ ይጀመራል!
ደም ለመስጠት አንድ ድንኳን ስር አገልግሎት ማግኘት ይቻላል! አጀንዳው ደም መስጠት ወየስ ተሰባበስቦ የሀገራችንን ሰላም የሚያደፈርሱ ክንውኖች ውስጥ መሳተፍ ነው
አብይን እና መንግስቱን ደም መስጠት ከለከለ ብላቸህ ስታለቃቅሱ አታፍሩም ግን፣ ማን አስተማረን እና፣ ማን አርአያ ሆነን እና፣ ማን ባህል እንዲሆነን አደረገው እና!
የፓርላማ አባላት ጭምር በየመንደሩ ወሬ እየለቃቀማችሁ ማህበራዊ ሚዲውን ማመሞቂያ ስታደርጉ ማየት እንዴት ያስተዛዝባል መሰላችሁ፣ ስንት ችግሮችን አይታችሁ እያለፋችሁ ነገር ግን ለወንበራችሁ የቀረቡ ሚመስሏችሁን ችግሮች እየመረጣችሁ መጠቀሚያ ልታደርጉ ትሞክራላችሁ፣ ህዝባችሁን ስሙ! በቃችሁ መንጫጫቱ!
እናንተም የፓርላማ አባላት ደም ስጡ! ድንኳን አቁሞ ደም መለገስ ይቻላል፣ እንኳን በጎው ተግባር ለክፉውም ትፋጠኑ የለ፣ ደም መስተት ከሆነ አጀንዳችሁ አሁንም አልረፈደም! አሁንም ይቻላል! የሚከልክላችሁ አካልም አይኖርም!