Get Mystery Box with random crypto!

'አዲስ አበባ የሚገባትን ብልፅግና ለማረጋገጥ በልበ ሙሉነት እንተጋለን!!' ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮ | Prosperity Party A.A ብልፅግና

"አዲስ አበባ የሚገባትን ብልፅግና ለማረጋገጥ በልበ ሙሉነት እንተጋለን!!"

ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ውጥን ነድፎ በሁሉም መስክ ህዝቡን አሰልፎ እየተረባረበ ይገኛል። ይህን ዓላማውን የተረዱ የውስጥና የውጪ ሀይሎች በተደጋጋሚ መሰናክሎችን ቢፈጥሩም ብልፅግና ተግዳሮቶችን ወደ ድል እየቀየረ ጉዞውን ቀጥሏል።

ኢትዮጵያ የህልውና አደጋ በተደቀነባት በህግ ማስከበሩ ወቅትም ጭምር ሀገርን ከመታደግ የህልውና ትግሉ ጎን ለጎን ልማቱንም በማስኬድ ከጦርነት ማግስት ሊደርስ የሚችለውን የከፋ ችግር ማቃለል ችሏል።

ብልፅግናን ማረጋገጥ የህዝባችንን ዘርፈ ብዙ ችግር እንደሚቀርፍ በማመን በከተማችን አዲስ አበባም በተለይም ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ጀምሮ በማጠናቀቅ ፓርቲው በምርጫ ወቅት ለህዝብ የገባውን የልማት ስራ ማከናወን እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ እየፈታ እንደሚሄድ ቃል በገባው መሠረት ቃሉን በተግባር እየፈፀመ ይገኛል።

የከተማችን ብልፅግና በአመራሩ ወይም በህዝቡ የተናጠል ጥረት ሳይሆን በተደመረ እርብርብ እውን እንደሚሆን ይታመናል። ህዝባችን በየአካባቢው ባሳየው የልማት ቁርጠኝነትም አዲስ አበባ የሚገባትን ብልፅግና ለማረጋገጥ በልበ ሙሉነት በመትጋት፤ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያን ደግሞ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ጉዞን በተግባር እናረጋግጣለን።