Get Mystery Box with random crypto!

''ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የቤት ችግር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የግልና የቡድን ፍላጎት | Prosperity Party A.A ብልፅግና

''ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የቤት ችግር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የግልና የቡድን ፍላጎት ለማሳካት ሲባል ቴክኖሎጂ በማበልፀግ ሂደት ውስጥ የሙያና የሃላፊነት እምነት በማጉደል የተፈፀመው ፀያፍ ተግባር ለህዝብ ጥቅም ሲባል እየተወሰደ ባለው እርምጃ የህዝብ ድጋፍ የታየበት ቢሆንም በአንፃሩ የተስተዋለው አሉታዊ እንቅስቃሴ ግን የሚያስተዛዝብ ነበር::

የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኝነትና የህዝብ ውግንና ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል:: በሌብነት ላይ ከተሰመረ ቀይ መስመር ማዶ የሚካሄድ ግብይት ግን ለሀገርም ለከተማው ማህበረሰብና ለተቋም ግንባታ ጠቃሚ ባለመሆኑ ትርፉ ትዝብት ነው::

የሌብነት አስተሳሰብን የመለወጥ ከባድ ትግል ቀልጣፋና ግልፅ የተግባር አውድ ለመፍጠር ሲባል በቴክኖሎጂ ለመደግፍ የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር እና ገንቢና ደጋፊ የህዝብ ተሳትፎ በማጎልበት ለጠንካራና የበለፅገች ሀገር ግንባታ አቅማችንን እናውል።''

አቶ መለሰ ዓለሙ
የአዲስ አበባ ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ