Get Mystery Box with random crypto!

ቃላችንን አላጓደልንም!! በማራኪ አያሌው ከአራት ዓመታት በፊት ሀገራዊ ለውጡ ሲበሰር የህዝባችን | Prosperity Party - ብልፅግና

ቃላችንን አላጓደልንም!!
በማራኪ አያሌው

ከአራት ዓመታት በፊት ሀገራዊ ለውጡ ሲበሰር የህዝባችን የለውጡን ፍሬዎች የማጣጣም ተስፋ ላቅ ያለ ነበር፡፡ የለውጥ አመራሩም ይህን የሕዝቡን ፍላጎት ለማርካት ሲረባረብ ቆይቷል፡፡ ህዝባችን በለውጡ ዘመን የእንጦጦ ከፍታ ከጫካነት ወደ ውብ ተፈጥሯዊ መዝናኛነት ሲቀየር ተመልክቷል፡፡ የቤተ መንግስት ቅጥር ጊቢ ለምቶና ተውቦ ሲበረከትለት፤ ጎርጎራና ወንጪ የልማቱ ተቋዳሽ ሰሆኑ አይቷል፡፡

የተቋማትና የምጣኔ ሃብት ሪፎርምን፣ የዜጎችና የሀገር ክብርና ፍቅር ከፍ ማለትን፣ ሳይፈልግ የተጫነበት የልዩነት ትርክት በአዲስ የአብሮነትና የወንድማማችነት ትርክት መቀየርን ሲመለከት ለሀገር አንድነት መሰረት እየተጣለ በመሆኑ ተስፋው ያልለመለመ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ የለም፡፡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በለውጡ ላደረጉት አበርክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም ኖቤል ሽልማትን በማበርከት አድናቆቱን ቸሯል፡፡

ከለውጡ በተቃራኒ የነበሩት አካላት ግን እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም፡፡ የሕዝቡን ፍላጎትና ውሳኔ አሜን ብለው መቀበል አልፈለጉም፡፡ አንድም በፍርሃት፤ ሁለትም እኔ ከሞትኩ … እንደሚሉት ሆኖባቸው ከውጪ ሃይሎች ጋር ጭምር ተቀናጅተው በሚለኩሱት እሳት ብዙ መከራ አስተናግደናል፡፡ የዜጎች ሞት፤ መፈናቀል፤ ግጭት፤ የመሰረተ ልማት ውድመት፣ ወዘተ ... ጉዟችንን አድካሚ፤ ድላችንንም በፈተና የታጀበ እንዲሆን አድርገውታል፡፡

አንዳንድ የውጪ ሃይሎች እነሱ በቀየሱልን መንገድ ብቻ እንድንራመድ በየምዕራፉ የነበረው ጉተታ አይዘነጋም፡፡ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ፤ በምርጫና በተለያዩ ጉዳዮች "እኛ ካልወሰንላችሁ" የሚለው መረን የለቀቀ ጣልቃ ገብነታቸው ከምኞት ባያልፍም ዋጋ አስፍሎናል፡፡ እኛ ግን በየግንባሩ የተከፈተብንን ዘመቻ በጋራ በመመከት እጣ ፈንታችን እንደ ሀገር በአንድ ላይ የተሰናሰለ በቀላሉ የማንሰበርና የማንበታተን ጠንካራ ሕዝብ መሆናችንን በዓለም አደባባይ አስመስክረናል፡፡

በነዚህ ዓመታት በአንድ በኩል ችግሮችን በመቀልበስና የሀገር አንድነትን በማስጠበቅ በሌላ በኩል ልማትን በማፋጠን የለውጥ አመራሩ ቃሉን ሳያጓድል ቀጥሏል፡፡ እንደ ሀገር ያነገብነው ራዕይ እና ሕዝቡ የሰጠን አደራ ከሚፈታተኑን ችግሮች በላይ ናቸውና የብልፅግና ጉዟችን ከስኬት ማማ ሳይደርስ አይቆምም፡፡ የሰፊውን ሕዝብና የሀገርን ተስፋ ያለመለሙትን የለውጡን መልካም ወረቶች እያካበትን የፍርሃት ቆፈን ለብሶ ከፊታችን የቆመውን ፀረ ለውጥ ሃይል አልፈንው እንሄዳለን፡፡
#Prosperityparty #prosperity