Get Mystery Box with random crypto!

በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን 'ቴዎድሮስ | ታታ አፍሮ -Tata Afro

በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን "ቴዎድሮስ እስኪነግሥ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሀምሌ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ከመጽሐፉ...

"...ቴዲ በሥነ-ግጥሙ ዘርፍ የነበረው ሀሳብን በተመጠነ ቃል የመግለጽና ለሰዎች በድምጹ የማቅረብ ልምዱ አድጎና ጎልብቶ እዚህ ደረጃ መድረሱ እጅግ አስገርሞኛል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ የመኖር ውበት የሚገልጽባቸው መንገዶች ልዩ ናቸው፡፡ አርቲስቱ ከፖለቲካ ነጻ መሆኑና ቀደምት ሀገሪቷን በከፍታ ላስጓዟት መሪዎች የሚሰጠው ክብር ከድምጻውያን መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚያሰልፈው ነው፡፡"

የቴዲ አፍሮ የቀድሞ አማርኛ መምህር ስለሺ ከበደ