Get Mystery Box with random crypto!

ደግ ጠፍቶ ባገር ፍቅራችን አለቀ የመምሬ ካባ ጥሏቸው ወደቀ .. መምሬ የጥንቱ የደብሩ ጉልላት | የኔ' ማስታወሻ ...✍️

ደግ ጠፍቶ ባገር ፍቅራችን አለቀ
የመምሬ ካባ ጥሏቸው ወደቀ
..

መምሬ የጥንቱ የደብሩ ጉልላት
በመስቀል ተዋግተው ለሃገሬ የሞቱላት
መኝታቸው እሾህ ጥልቅ ዋሻ ቤታቸው
ልብሳቸው ደበሎ ሰኔል ነው ቆባቸው
:
የዘንድሮው አባ ..
የዘንድሮው አባ ፂማቸው ዠርጋጋ
ቤታቸው G+ መኝታቸው አልጋ
.. እንጃ ብቻ



ትውስ ያሉኝ እለት የጥንቱ መምሬ
ሳወጣና ሳወርድ ጊዜውን አስ'ሬ
ይነጋል ይመሻል ባሳብ ተወጥሬ

:
..
እንዲያው ለምናልባት
እግዜሩ ዝም ያለ ቢጠራ ቢጠራ
ወጥተን ይሆን እንዴ ከሰው 'ነት ተራ ??


ሃይሚ ነኝ ባለ ማስታወሻዋ

@poethaymi