2022-01-24 00:26:37
ከሀብት ሁሉ ትልቁ ሀብት ልብን መስጠት ነው።
ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታ ራስህን ነው።
ሀገር እንዳትጠፍ ትልቅ ነገርን አታጥፍ።
ሕይወት ሁለት ጎን አላት ማግኘት እና ማጣት ፣ማጣትም በራሱ ሁለት ጎን አለው የምታገኘውን ነገር ማጣት እና የማታገኘውን ነገር ማጣት።
ሀብታሞች የተፈጥሮን ሕግ ሰብራችኃል። በሚሰራበት ሰዓት ትሰራላችሁ በሚተኛበትም ሰዓት ትሰራላችሁ። ምነው ስትባሉ ድህነትን ለማጥፍት 24 ሰዓት እንሰራለን ትላላችሁ ። ድህነትንስ ታሸንፉታላችሁ ሳታውቁት ግን ለውስጣችሁ ሰላምና እና ደስታ ትሸነፉላችሁ።
ጭቃው በሸክላ ሰሪው እጅ ላይ ነው ሰው በአምላኩ እጅ ላይ ነው እንደወደደ አድርጎ የሚሰራው ፈጣሪ ነው።እኛ ማድረግ ያልቻልነውን ፈጣሪ ያደርግልናል ።
ይቅርታ ልጠይቃት ይገባል እኛኮ ምንም አላደረግንም. እሷን መሰላታ..።
ሠማይና ምድር የቆመው በቃል ነው።ያ ቃል ለኛ ጥበብን ይሰጠናል ልክ ለነዚህ እጆች እንደተሰጡት.አብዬ ከዚህ በኅላ ጥበብ ከሰጠህ ጋር አትታገል እርሱ እራሱ አንድያ ልጁን ሰጥቶናልና።
ትክክለኛ ማሸነፍ በሰው ዘንድ የእራስን አመለካከት ማጋባት ነው። ከተጣላህ ወይም ከሸሸህ አንተ ተሸንፈሀል ከራስህም ከሰውም ጋር ተጣልተኃል ።አንተ እራስህን ለፍቅር ብታዋርድ አንተ ከፍ ከፍ ትላለህ ስለዚህ ትንሽ አቀርቅር።
ጥሩ በልክ አይመዘንም ፣ ልክ ነው በጥሩ የሚመዘነው።
ተፈጥሮን በተቃውምን ቁጥር፣ ስልጣኔ ባበዛን ቁጥር፣ ችግራችን ይበዛል ችግራችን ደግሞ የምንወዳቸውን ነገሮች ያሳጣናል።
አምላክህን ደስታህን በቅንነት ብትጠይቀው ይሰጥሀል። ብቻ በቤትህ በሀቀኝነት ኑር።
ተስፍን የሰጠ የታመነ ነው።
ከረቡኒ ፊልም
ውብ አሁን
@EthioHumanity
@EthioHumanity
461 viewsHaileab ቶ, 21:26