Get Mystery Box with random crypto!

ፍራ ሰምቶ እንዳልሰማ ፣ ቢሆን ኖሮት ጆሮ አይቶ እንዳላየ ፣ ቢደበቅ ከ ጓሮ አፍ ኖሮት ፀጥ ቢል | ግጥምን በዜማ📚🎻

ፍራ

ሰምቶ እንዳልሰማ ፣ ቢሆን ኖሮት ጆሮ
አይቶ እንዳላየ ፣ ቢደበቅ ከ ጓሮ
አፍ ኖሮት ፀጥ ቢል ፣ መናገር ባይሻ
ፈርቶህ እንዳይመስልህ ፣ ይህን ጊዜ ሀበሻ
ጀግና የጀግና ልጅ ፣ የሰው ዘር መነሻ
ሲሸሽ ሊያሳጣህ ነው ፣መነሻ መድረሻ ።


ዝም ሲል ሊያደምጥህ ፣ ስተትክን ሊረዳ
እያየ እንዳላየ ፣ ሲደበቅ ከ ጓዳ
አንድ እየሆነ ነው ፣ ዘመድና ባዳ ።


ጆሮው እየሰማ ፣ ቢመስልህ ደንቆሮ
ፀጥታው ካየለ ፣ አንድ ሁለት ቀን ቆጥሮ
ሊያጠፋህ ነው ፣ ቀብሮ ።

ስለዚህ ፍራ

#ኪሩቤልዮናስ

@yegtm_hywet
@amharic_poet