Get Mystery Box with random crypto!

የውድቀቴ ሚስጥር ፈጣሪ ሰዎች እንዲገዙበት አክብረው እንዲኖሩ እለት በ እለት እኔን ብቻ አምልክ | እግር ኳስ Meme™

የውድቀቴ ሚስጥር
ፈጣሪ ሰዎች እንዲገዙበት
አክብረው እንዲኖሩ እለት በ እለት
እኔን ብቻ አምልክ አትይ ወደሌላ
ጠንካራ ሁንና ማተብህ ሳይላላ
አትስረቅ የሰው ላብ አትንካ ብያለው
በሰው የከበረ ሲሞትም በሰው ነው
አስር ትዛዝ አዞ እዳበቃ ጌታ
ለሰው ኖሮ ሞተ በሰዎቹ ፋንታ
ገዳዩ አያቴ ወልዶት አባቴን
አባቴም ወለደኝ ሊተካኝ እኔን
ያን ጊዜ አያቴ ሰቀለው በ መስቀል
አባቴም ቀጠለው ሰውን በማሰቀል
እኔም ተከተልኩት ያባቴን መንፈስ
የህይወት መስመሬን ህግ በመጣስ
በ ዝሙት ህይወት ውስጥ ስጋዬ ደለበ
በውሸት ዓለም ውስጥ ዝናዬ አበበ
የምድሩን ገንብቼ ከናድኩ የሰማዩን
ፈጣሪዬ ቢለኝ ቢጠይቀኝ ለምን
መልስ የሌለኝ ሰው ነኝ የሆንኩኝ ነኝ ብኩን
LISE DECH SOFI YE LASTAWA
@LISEDECHSOFI

@yegetemkalat
@poem_merry