Get Mystery Box with random crypto!

ሳይጀመር ለቀረ ለባከነ ፍቅር ጥንስሱን መተው ነው | እግር ኳስ Meme™

ሳይጀመር ለቀረ
ለባከነ ፍቅር
ጥንስሱን መተው ነው
ሁሉም እርግፍ ይበል
ሁሉም ነገር ይቅር
መ..ተ..ው ለለመዱ መተው ምንም ነው
የኔና አንቺ ፍቅር ሳይጀመር ያለቀው ምክንያቱ ምንድን ነው
ጀመሩ ስንባል
እፍ አሉ ስንባል ባንዴ ለተቋጨው
የኔና አንቺ ፍቅር ምን ነበረ ምርጫው

ሳታውቂኝ አወኩሽ
እያደረ በዝቶ ያንቺም ፍላጎትሽ
ተውሽኝና ተውኩሽ
ገና ከጅምሩ
ተራርቀው ቀሩ
ተብሎ ቢወራ ለመንደር ለሃገር
ምክንያቱን አያውቁት
ምክንያቱን አናውቀው የኔና አንቺን ነገር

ሳንጀምር ጀመርነው በደስአለኝ ዲስኩር
በደስአለኝ ምናብ
ለጊዜያዊ ምቾት ለጊዜያዊ ድባብ

ዮኒ
ኣታን @Yonny_Athan

@poem_merry
@yegetemkalat