Get Mystery Box with random crypto!

ትልቅ ለውጥ ትልቅ ለውጥ በትንሽ አስተሳሰብ አይፈጠርም። በህይወትህ ላይ ምን እንዲለውጥ ትፈልጋለ | እግር ኳስ Meme™

ትልቅ ለውጥ
ትልቅ ለውጥ በትንሽ አስተሳሰብ አይፈጠርም። በህይወትህ ላይ ምን እንዲለውጥ ትፈልጋለህ ? መጀመሪያ አንተ እንዲለወጥ በፈለከው ነገር ልክ መለወጥ አለብህ። ህይወትህ ላይ ነገሮች ምርጥ እንዲሆኑ ትፈልጋለህ አንተስ በዛ በፈለከው መጠን ምርጥ ነህ?
የብዙ ሰው ችግር ይሄ ነው። ህይወታቸው በአንድ ለሊት እንዲለወጥ ከመፈለግ ውጪ እነሡ ለለውጥ ዝግጁ አይደሉም። ሀብታም መሆን ፈልገህ ነገር ግን ሀብት የሚመጣበትን አማራጭ ካልፈለክ ሀብታም ለመሆን የሚከፈለውን ዋጋ ካልከፈልክ ትልቅ እሚባል ለውጥ እንዴት ታስተናግዳለህ?

ህይወት የምትለወጠው አልጋህ ላይ ተጋድመህ በምታልመው ህልም ሳይሆን ህልምህን ለማሳካት በወሰንከው ውሳኔ ልክ ነው። ለውጥ የሚመጣው አንተ ለመለወጥ ስትዘጋጅ ነው። ለለውጥ ዝግጁ የሆነ ሠው የትኛውንም ዋጋ ይከፍላል። ዋጋ መክፈል ካቃተህ ከልተዘጋጀህም በቃ እመን። ሰበብ አትፈልግለት ዋጋ ላለመክፈልህ።

አንድ ምግብ ቤት ገብተህ ለመመገብ እኮ ፍላጎት ብቻውን በቂ አይደለም የምትገለገልበትን የምግብ ዋጋ መያዝ አለብህ። የምር ምግቡን መብላት ከፈለክ የምግቡን ዋጋ መክፈል አለብህ። አበቃ ሰበብ አያስፈልገውም። የምር አንድን ነገር ከፈለከው የምር ዋጋ ትከፍልለታለህ። የምር ካልፈለከው ደግሞ ሰበብ ስትደረድር ትኖራለህ አብዛኛዎቻችሁ ሰበበኞች ናችሁ። አዎ ናችሁ። ከስኬት ከለውጥ ከስልጠና ለመራቃችሁ እናት ፣ አባት ፣ ጓደኛ ፣ የሀገር ሁኔታ ፣ የገንዘብ ማጣትን ሰበብ ታደርጋላችሁ። ይሄ ምንም ምክንያት አይሆንም። ምክንያቱም ዋጋ ያልከፈላችሁበት ነገር እጃችሁ ላይ ቢገባም ታቀሉታላችሁ እንጂ አታከብሩትም። ስለዚህ የትኛውም ትልቅ የሚባል ለውጥ ትልቅ የሚባል ዋጋን ያስከፍላል። በዘመኑ ዋጋ የማይከፍል ሰው ምንም እየሰራ እና እየተንቀሳቀሰ ያልሆነ ሰው ነው አበቃ። ስለዚህ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ሁኑ ከዛ ለውጥ ምን እንደሆነ በደንብ ታዩታላችሁ እውነት።

@buchula36

@yegetemkalat
@poem_merry