Get Mystery Box with random crypto!

የጭስ ወዳጅ ቁስል ተቆራኝቶት ህመሙ ቅጥ አጥቶ ሚካፈለው ወዳጅ የሚናገርበት አንደበቱ ጠፍቶ። ምስ | እግር ኳስ Meme™

የጭስ ወዳጅ

ቁስል ተቆራኝቶት ህመሙ ቅጥ አጥቶ
ሚካፈለው ወዳጅ የሚናገርበት አንደበቱ ጠፍቶ።
ምስቅልቅል በሆነ በጨለማ ዓለሙ
እዚ እዛ ሲማትር ተዋግቶ ከሀሳቡ።
ቁና ሲተነፍስ በሲቃ ውጥስ ሆኖ
ህመሙ ወሰን ጠፍቶት ያለው ተስፋ በኖ።
በጣቱ ከያዘው ከአጥፊው ስለት ማልዶ
በጭስ ተደብቆ ማንነቱን ከድቶ።
ሲያቦነው ሲያቦነው ከጭስ ጋር ሀሳቡን
ሊታረቅ ሲማልድ እንዲሰጠው ቀልቡን።
የነበረው ተስፋ የነበረው እምነት
እንዳያድግ ሚያረገው በዝቶ በእየሄደበት።
በጭለማ ተውጦ ብርሀኑ ኮብልላ
ነጠቅ መሰል ሆና ለሌላው ታድላ።
ምርጫ ያልነበረው ያ ምስኪን አንድ ሰው
ለጭሱ እሱነቱን አየውት ሲያውሰው።
ጭሱም እህ እያለ ሀሳቡን ሲያደምጠው
ሰምቶ ውሎ ሰንብቶ ለንፋስ ሲልከው።
ንፋሱም እንዳሻው በሄደበት ሁሉ
ጭንቀቱን ሲያድለው ባለው ዐቅም ለኩሉ።
ቅብብሎሽ ሆኖ የዛ ምስኪን ስቃይ
ጭሱ ለንፋሱ ንፋሱ ለሰማይ።
የሶስትዮሽ ወሬ አድርጎት ውጥረቱን
በጭስ ተደብቆ አየው ማንነቱን።

#ኪሩቤል_አሰፋ

@poem_merry
@yegetemkalat