Get Mystery Box with random crypto!

ብትስቅ ምን አለበት ? ብትስቅ ምን አለበት አለም ላይ እንደሆን÷ አንዳች የለህ ጉልበት። ስት | እግር ኳስ Meme™

ብትስቅ ምን አለበት ?

ብትስቅ ምን አለበት
አለም ላይ እንደሆን÷ አንዳች የለህ ጉልበት።
ስትወድቅ ስትነሳ÷ ቆምኩ ስትል ስትወድቅ
ጨለማ ነው ስትል ÷ብርሀን ጎህ ሲቀድ
አይኖችህን መግለጥ ÷ ደግሞም ለቀን ማቀድ
መኖር ባትፈልግም÷ ሞትን አለመፍቀድ
ዘውትር ቀኖችህ ላይ
ሳቆችህን ትተህ ÷እንቦችህ ላይ መውደቅ
ሆኗል ያንተ መንገድ ።
:
ቢሆንም ግን ይህ ሁሉ
ውሉ ያልታወቀው÷ መንገድህ ውበቱ ።
አንተ ግን ስህተትህ
ውሉ ባይታወቅ መንገድህ ቢጠፋ
እንዴት ግን አስችሎህ
እንዴት ፈገግታህ ላይ ትቆርጣለህ ተስፋ።
:
አንተ
ለመሸከም ሁሉን÷ የሌለህ አቅሙ
ልብህ ቢያለቅስ እንኳን ÷ብትስቅ ለአመሉ
እስቲ በል ንገረኝ ምንድነው ችግሩ
ከእለታት አንዳንዴ ጥርሶችህ ቢታዩ
የእለት ወዳጆችህ እንቦችህስ ቢያርፉ።
:
በቃ ኢሀው ነው
ነገሮች ጨልመው ÷ቢጠፋቸው ውበት
ሀዘን ቢከብድህም ÷ብታጣ አቅም ጉልበት
እንዲያው ግን አንዳንዴ÷ ብትስቅ ምን አለበት ??

ኬቲኤል

@poem_merry
@yegetemkalat