Get Mystery Box with random crypto!

ለመፍረድ_አንቸኩል     ዶክተሩ ስልክ ይደወልለትና እየሮጠ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል፡፡ሆስፒታል ከ | እግር ኳስ Meme™

ለመፍረድ_አንቸኩል

    ዶክተሩ ስልክ ይደወልለትና እየሮጠ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል፡፡ሆስፒታል ከደረሰ ቦሀላ ልብሱን በፍጥነት ቀያይሮ ወደ ኦፕራሲዮን ክፍል እየተጣደፈ ሲሄድ መግቢያ በሩ ላይ ቆሞ ይጠብቀው የነበረ የታማሚው ልጅ አባት
እንዴት እዚህ ለመድረስ ይህን ሁሉ ሰአት ይፈጅብሀል ዶክተር ? የሰው ህይወት ግድ አይሰጥህም?በጣም ዘገየህ ሲለው
ዶክተሩም በፈገግታ ይቅርታ ሆስፒታል ጊቢ ውስጥ አልነበርኩም ስልክ ከተደወለልኝ ቦሀላ ግን አቅሜ በፈቀደ መጠን በፍጥነት ለመድረስ ሞክሬያለው ተረጋጋ አለው::

ተረጋጋ ትለኛለህ? ታሞ ሊሞት እያጣጣረ ያለውኮ የኔ ልጅ ነው እንዴት ተረጋጋ ትለኛለህ? ያንተ ልጅ ቢሆን እንደዚህ ትላለህ? አንተ በመዘግየትህ ልጄ ሊሞትብኝ ነው ትንሽ አታስብም? ብሎ ሲጮህበት
ዶክተሩ አሁንም ፈገግ እያለ

ዶክተር የሰውን ልጅ ህይወት ሊያረዝምም ሊያሳጥርም አይችልም አፈር ነንና ወደ አፈር መመለሳችን አይቀርም አሁን ተረጋጋ እኔም ስራዬን ልስራበት ብሎ ወደ ሰርጀሪ ክፍል ገብቶ ለተወሰኑ ሰአታት የህፃኑን ቀዶ ጥገና ካከናወነ በሁዋላ ወደ ውጭ ወጥቶ በፈገግታ የልጁን አባት እንኳን ደስ አለህ   ልጅህ ሰርጀሪ ከተደረገለት ቦሀላ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል ከዚህ በሁዋላ የሚያስፈልግህ ነገር ካለ ነርሷ ትረዳሀለች ብሎት እየሮጠ ከሆስፒታሉ ወጣ፡፡
ሰውዬው በሰማው መልካም ዜና ቢደሰትም የዶ.ሩ ሁኔታ ግራ ስለገባው ነርሷን ዶ.ሩ ምን ሆኖ ነው እንዲህ የተዋከበው? ብሎ ሲጠይቃት
ዶ.ሩ ትላንትና ልጁ በመኪና አደጋ ሞቶበት ቀብር ላይ ነበር ያንተ ልጅ ህመም አደገኛ ስለነበር እንዲያክመው ደውለን ጠርተነው ነው አሁን ያንተን ልጅ ካዳነ በሁዋላ የልጁ ቀብር ላይ ለመድረስ ነው እየሮጠ ያለው  ስትለው
ሰውዬው ድርቅ ብሎ ቀረ

የሰው ልጅ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሆነ ሳታውቅ አትፍረድ ...

  ካነበብኩት ነው ቸር ጊዜ ።

ከወደዱት ያጋሩ

@yegetemkalat
@poem_merry