Get Mystery Box with random crypto!

 ሳያጠፋ ከተፈረደበት ። ቷ ቷ ቷ፡ ስነስርዓት ! ፍርዱ ፡ ቤት ፡ፅጥ፡ አለ | እግር ኳስ Meme™

 ሳያጠፋ ከተፈረደበት ።
ቷ ቷ ቷ፡ ስነስርዓት !
ፍርዱ ፡ ቤት ፡ፅጥ፡ አለ
አስፈራጅ ቀጠለ ፦
በቆመው፡ ተከሳሽ ፊትለፊቶ፡ ባለው
በወንጀሉ፡ ብዛት፡ፍርዱ፡ግን፡ምንድን፡ነው ?
ቀጠለ፡ ፈራጅ ፦ እንዲህ፡ሲል፡ጠየቀ
ጥፋቱ፡ምንድን፡ነው ?
"እስከሚያዝ፡ድረስ፡ምን፡ያልሰራው፡አለ
የሞተ፡ሲያስነሳ፡እውሩን፡ሲፈውስ፡ሁሉምሰው፡ዝም፡አለ
አስማተኝነቱን፡በሰንበት፡ቀጥሎ
ከተሰበሰቡት፡ቃሉን፡ከሚሰሙት፡፦
መሀል፡እቺን፡ሴት፡ነጥሎ
ወደእርሱ፡ጠራና፡እጁን፡ሲጭንባት፦
ቀጥ፡ብላ፡ቆመች፡ደዌው፡ሄደ፡ጥሏት
ምንምን፡አላስከፋን፡እንሰራለን፡እኛም፡የበለጠ፡አስማት
ግን፡ክቡር፡ፍርድቤት፡እርሱን፡ከእርሶ፡ፊት
እንድንገትረው፡ያደረገን፡የበለጠው፡ምክንያት
ያለወንድልጅ፡ዘር፡በናቴ፡ማህፀን፡በድንግልናነው
የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ሆኜ፡ምድር፡የመጣሁት
ሲለን፡ነው፡የበቃን፡ክቡር፡ዓቃቢ፡ህግ"
በለው፡ተናገሩ፡
ወጣ፡ብለው፡ዳኛው፡ከህሊናቸው ጋር፡ጥቂት፡ተማከሩ
እንደተመለሱ ፤ ቷ ቷ ቷ
እ እ እ መፍረድ ከበዳቸው
ጠብ ጠብ ማለት ጀመረ ላባቸው ከግንባራቸው
የሆነ ነገር ግን ከበዳቸው ለማን ይበይኑ
ክርስቶስ ነው ተከሶ የቀረበውከፊታቸው።
እውነትን ለመፍረድ ግራው ከቀኙ ጠፋባቸው
እንዲህም አለ ልባቸው ተዋወቁ ከፈጣሪ
ክርስቶስም መንገድ ሆነላቸው
" እኔን ለምን
እኔን ለምን በዚህ ዘመን
ሌላ ጌዜ የማይከብደኝ ይህ ሰራዬ
አሁን ለምን ጥሎኝጠፍ ከስጋዬ
ምን አገደኝ እንዳልሰራ
ማንን ልመን ምንስ ላውራ
ለዚህች ቀን እንድኖር ነው ሳትገድል ያቆየኸኝ
በቃ የህን ብዬ ያሉትን ይበሉኝ "
"እ " ጉሮሮውን ጠረግ አደረገው
"እዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁ"
የከሰሱት ያላመኑት ያልገባቸው ያላወቁት
ጲላጦስ ላይ የተቃውሞ የብስጭት
ድምፃቸውን እያሰሙ እንዲህብለው ተናገሩት
"ይህ ደፋር ላይ ብይን በይን
ምንም ጥፋት እንዳልሰራ ለሱ አትወግን
ብይን በይን (3) ህግይከበር (3) "
በአለም ላይ ታይቶ ም ተገምቶ ም
ፈራጁ ጲላጦስም ሆነ
የክርስቶስ ከሳሾች አይተውት የማያውቁት
ህዝብ ነበር የተሰበሰበው
ጲላጦስ ጨነቀው
ብዙ ብይን እስከዚህች ቀንና
እስከዚህች ሰአት በስልጣኑ ፍርድን ፈርዷል
በዚህች ቀን ግን ነብሱን ያወቀ መሰለው
ክርስቶስን አይቶ ከስጋው ቀለለው
ህዝቡ ግን ገረመው ከመበየን ይልቅ
ከሱ ያቆሙትን እንዲህ ሲል መጠየቅ
" በናንተ ፍላጎት ህጉን ከሻራችሁ
ምን ይቀጣ ይህሰው ምንስ ላርግላቹ "
እሱን ስቀልና በርባንን ፍታልን
ከዚህ ደፋር ይልቅ እርሱ ነው ሚሻለን
ነፃነት ለበርባን(5)
ከቅድሙ በላይ ጨነቀው ጲላጦስ
ሰውም ግርም አለው ፍርደኛው ክርስቶስ
ክርስቶስም ለጲላጦስ
በፈገግታ እንዲህ አለው
"ስለኔ አትጨነቅ ያሉህንም አርግላቸው" ።

እስቲማነው እ ከክርስቶስ ፍቅር እኔን
የሚለየኝ የተኛው ነብይ ነኝ ባይ ነው
ዘመኑን በሙሉ ልክ እንደ ቀንድ አውጣ
ተኝቶ ተኝቶ ዛሬ ሰለ ክርስቶስ በየ ስጋ መሽጫውና
በየ የባስ ፌርማታው በየ ቅድስና በሌለው በተቀዳደ ልብ ሆኖ ስላ ዳነኝ ሰለእርሱ እንደመጣለት በድፍረት ቃሉን የሚሰብከው
የኔ መድሀኒት የእርሱ ደምና ስጋ ነው
ዋ በየመንገዱ በየ ስልጣኑ በየ ባስ መጠበቂያና በየ ባቡርውስጥ እየገባችሁ የምትዘባርቁ መናፍቆች ሰይጣን ሲጋልባችሁ በስመ አብ በሉ ፀጋችሁን አታክፋፉ ።

ረቂቅ መላኩ