Get Mystery Box with random crypto!

የእመቤታችን ዕርገት ... በአርመን ኦርቶዶክስ ዝማሬ ላይ በዕርገቷ ጊዜ እንዲህ ይዜማል፡- ዛሬ | ዮሐንስ ጌታቸው

የእመቤታችን ዕርገት

...
በአርመን ኦርቶዶክስ ዝማሬ ላይ በዕርገቷ ጊዜ እንዲህ ይዜማል፡- ዛሬ ሰማያውያን የመንፈስ ቅዱስን ማደርያ ወደ ሰማይ አመጡ። ወደ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ያስገቧት ዘንድ፤ እኛ ልንደርስበት በማይቻለን የሥላሴ ክብር በሚገለጥበት ማደርያ በዘለዓለማዊቷ ድንኳን ሰማያውያን ምሥጢር ትሳተፍ ዘንድ አመጧት። “ዛሬ ሰማያዊያን መላእክት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ አካል ዐሣረጉ፣ በሰው ቋንቋ ሊነገር የማይቻለውን ሰማያዊ ዘለዓለማዊ ደስታ ትሳተፍ ዘንድ በመላእክት መካከል አስቀመጧት” በማለት በግሩም ዜማ የድንግሊቱን ዕርገት በማድነቅ ዝማሬ ያቀርባሉ፡፡ በዲያብሎስ ምክንያት ከዚህ ምሥጢር ርቀው በሕይወታቸው ፍሬ የታጣባቸው የዚህ ዓለም ኑሮን ብቻ የሚወዱ የአስተሳሰብ ድቀት ሰለሠለጠነባቸው ከድንግሊቱ የዕርገት ዜና ርቀዋል። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ርቱዓ ሃይማኖትም የድንግሊቱን ዕርገት እንዲህ ይላል፡- አባ ብንያምም ለአንጥያኮስ ሲነግረው “የማርያም ሥጋ እንደጻድቃን ኹሉ በመቃብር አለ የሚል፤ ሥጋዋ በሰማይ እንዳለ ነፍሷም ከሥጋዋ እንደተዋሐደ የማያምን በነፍሷም በሥጋዋም ከሦስቱ ሰማያት በላይ በመንግሥተ ሰማይ እንዳለች ወደ ወደደችውም የምትጎበኝ በሰማይም በምድርም ሥልጣን እንዳላት በጸሎቷ የሚታመኑ ፈቃዷንም የሚያደርጉ እንደሚድኑ ይህን የማያምን ዕጣው በልጇ ስም ካልተጠመቁት ወገን ይኾናል። በጭቃ ከተሠሩ በውጭ ካሉ ቤቶች ይልቅ በወርቅ የተለበጠ የንጉሥ ቤት እንደሚበልጥ ኹሉ የድንግል ማርያም ክብርም ከኹሉም ፍጥረት ይበልጣል” አለ በማለት ሊቁ የአባ ብንያምን ቃል እንሥተው የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት በክርስቲያኖች ዘንድ ሊታመን እንደሚገባ ገልጾልናል። የኢየሩሳሌሙም ጳጳስ ጢሞቲ የእመቤታችንን ዕረፍትና ዕርገት እንዲህ ገልጸዋል፡- “ድንግል እስካኹን ድረስ ሟች ያለመኾኗ ምክንያት በርሷ ውስጥ ያደረው ጌታ ወደ ማረጊያ ክልሎች ስለወሰዳት ነው” በማለት ሞት በሌለበት በዕረፍት ስፍራ ልጇ ያሣረጋት መኾኑን አስተምረዋል። ሌሎችም ሊቃውንት ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢሩሳሌም፣ የብኅንሳው አባ ሕርያቆስ፣ ዮሐንስ ዘደማስቆ አብራርተው ስለ ዕርገቷ ገልጸዋል፡፡