Get Mystery Box with random crypto!

ፅርሀ አርያም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ phnotesedksenbettmhrtbet — ፅርሀ አርያም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ phnotesedksenbettmhrtbet — ፅርሀ አርያም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን
የሰርጥ አድራሻ: @phnotesedksenbettmhrtbet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 317
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ተዋህዶ
የተለያዮ ኮርሶች ሚሰጡበት
ስለ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ወቅታዊ መረጃዎች

ለተዋህዶ ልጆች በመላክ ሀላፊነታችንን እንወጣ
@Emamlaknn

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-06-29 18:40:58 Channel photo updated
15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-29 18:40:33 ትሕትና የአገልግሎት መሠረት ነው፡፡ሌሎችን አገልግሎቶች የሚያቃና ትሕትና ነው፡፡ የትሕትና መጉደል አገልግሎትን ያጠፋል፡፡ በአገልገሎት ላይ የማሰናከያ ድንጋይ ይሆናል፡፡ በአገልግሎት ትሑት ለመሆን ማን እንደሆንን፣ ከየት እንደመጣን ወዴትም እንደምንሄድ ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ አገልጋይ የበሰለ መሆን አለበት፡፡ሓላፊነት የሚሰማው የተገባም መሆን አለበት፡፡ለአገልግሎቱ ጥብቅ መሆን አለበት፡፡ ታማኝ አገልጋይ በወንጌል በተሠጠው መክሊት ያተረፈ እንደሆነ ተመስክሮለታል፡፡/ማቴ25፡14-30/ አገልጋይ በመንፈስም በሥነ ልቡናም የበሰለ መሆን አለበት፡፡ በሥራና በድርጊት የተረጋጋ መሆን አለበት፡፡ ችግርን በመንፈሳዊ ጥንካሬ መወጣት ይጠበቅበታል፡፡ በሥነ ልቡና የተረጋጋ ፣ያመነውን የሚያውቅ፣ የሚሠራውን የሚያውቅ የሚያገለግለውን የሚያውቅ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ራሱን የሚገዛ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነውና ሓላፊነቱን በትክክለኛ መንገድ የሚወጣ ይሆን ዘንድ ብስለት ያስፈልገዋል፡፡ መታዘዝ ልክ እንደትሕትና ሁሉ የአገልግሎት መሠረት ነው፡፡አገልጋይ ሁልጊዜም ታዛዥ መሆን ይጠበቅበታል፡፡መታዘዝና ትሕትና እርስ በርስ የተያያዙ ናቸው የአንዳቸው መኖር ለሌላቸው አስፈላጊ ነው፡፡ አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ትሑት አገልጋይ ታዛዥ ነው፡፡ትሕትና ሲጎድለን መታዘዝም ይጎድለናል፡፡
309 viewsMel፰ Yemamlak, 15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-08 12:19:18 ዓርብ
#ቤተ ክርስቲያን ትባላለች

ዓርብ፦ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች። ጌታችን ከልደቱ እስከ ሞቱ ያደረገው የማዳን ጉዞ በሙሉ የተፈጸመው ዓርብ ነው። “ወይቤ ተፈጸመ ኵሉ” እንዲል። ዓርብ የቤተ ክርስቲያን ሁለመናዊ ምስጢር የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች።

ማለትም ዓርብ ለቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆኑ ዋና ዋና ምስጢራት ተሟልተዋል። ለምሣሌ የመስቀል አዳኝነቱ ከእርግማንነቱ ተለይቶ ታውቋል፤ የሕንጻዋ መሠረት ቀራኒዮ ተተክሎላታል፤ ሥጋ
መለኮት የምትፈትተው በቀራኒዮ ተቆርሶላታል፤ ልጆቿን ከማኅጸነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምትወልድበት ማየ ገቦ ፈስሶላታል። ስብከት፣ ትምህርት፣ ተአምራት፣ ትንሣኤ
ተደርጎላታል። ይህንን ሁሉ ምሥጢር ያገኘችው በዕለተ ዓርብ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ተባለች። የዓርብ ትርጓሜው የሥራ መክተቻ፣ ምዕራብ፣ መግቢያ ማለት ነውና። ኤፍ2፤19፤ራዕ1፤6-8
411 viewsMel፰ Yemamlak, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-08 12:19:18

#ተነስታል_ረቡኒ

እንቅልፍ የለኝ ዛሬስ በምንጣፌ
ከሞት መዳፍ ከአጋንንት ተርፌ
እገሰግሳለሁ ጨለማን ሳልፈራ
ከመስቀል አውርደው ከቀበሩት ስፍራ
#ክርስቶስ_ተንስዓ_ሙታን_ሞተ_ወኬዶ_ለሞት
#ለእለ_ውስተ_መቃብር_ወሀበ_ሕይወት#ዘለዓለም_እረፍተ
#አዝ
ነፃ አውጥቶኝ ከአጋንንት እስራት
ጤናን ሰቶኝ የታደገኝ ከሞት
ውለታው አለብኝ እጅግ የበለጠ
ከጠላት መንጋጋ ነፍሴን ያስመለጠ
#ክርስቶስ_ተንስዓ•••••••
#አዝ
ስሙኝ ቃሌን ደቀ መዛሙርቱ
ሽቶ ይዤ ስሄድ በጥዋቱ
መግነዙ ብቻ ነው በመቃብር ያለው
ተነስታል ኢየሱስ እንደተናገረው
#ክርስቶስ_ተንስዓ••••••
#አዝ
መመላእክቱ ነጭ ልብስ ለብሰው
ከመቃብሪ አየው ተቀምጠው
ከሙታን መካከል አትፈልጉት የለም
ተነስታል ረቡኒ ጌታ መድሃኔአለም
#ክርስቶስ_ተንስዓ•••••••

#ዘማሪት_ፋሲካ_መኮንን

ተቀላቀሉ!! @Melsh21
362 viewsMel፰ Yemamlak, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-08 12:19:18 ረቡዕ
ከትንሳኤ እሑድ ቀጥለው ያሉት ዕለታት ሰሙነ ፋሲካ ወይም ትንሳኤ እየተባሉ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜ አላቸው፡፡ በዚህም መሰረት ረቡዕ አልዓዛር በመባል ይጠራል፡፡
ከሞተና ከተቀበረ አራት ቀን በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላሥነሣው፣ አልዓዛር መታሰቢያ የእርሱንም ተነሥቶ በማየት በጌታችን ብዙ ሕዝብ ስለአመነበት ቀኒቱ «አልዓዛር» ተብላ ትታሰባለች፡፡
ዮሐ. 11-38-46

ሀሙስ
ይህቺ ዕለት ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ፤›› ተብሎ ቃል የተገባለት የአዳም ተስፋው ተፈጽሞ ከነልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ኾና ‹የአዳም ኀሙስ› ወይም ‹አዳም› ተብላ ትከበራለች::
ሉቃ. 24-25-49
288 viewsMel፰ Yemamlak, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-08 12:19:18 #ቶማስ

ማክሰኞ፦ ቶማስ ይባላ ል። ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ የጌታችንን ጐን የዳሰሰበትና እጁ የደረቀችበት እንደገና መልሳ የዳነችበት መታሰቢያ ነው። ለቶማስ ታሪክ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ዕለቱ ቶማስ ይባላል። ምንም እንኳን ታሪኩ የዳግማይ ትንሣኤ ቢሆንም አበው ታሪክ
ከታሪክ እንዳይደራረብ ብለው ነው። ዩሐ20፤27-29
275 viewsMel፰ Yemamlak, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-08 12:19:17 #ማዕዶት፦

የትንሳኤ ማግስት ሰኞ ማዕዶት በመባል ይታወቃል ማዕዶት ማለት (ዐደወ-ተሻገረ) ከሚል የግእዝ ግስ የተወረሰ ሲሆን በጥሬው "መሻገር" ማለት ነው:: ይሕም በደመ ክርስቶስ ተቀድሰን: በትንሳኤውም ድኅነት ተደርጐልን መከራን: መርገምን: የኃጢአትን ባሕር: አንድም ባሕረ እሳትን መሻገራችንን ያመለክታል::

✥ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ
*ከባርነት ወደ ነጻነት
*ከጨለማ ወደ ብርሃን
*ከሞት ወደ ሕይወት
*ከኃጢአት ወደ ጽድቅ
*ከሲዖል ወደ ገነት
*ከገሐነመ እሳት ወደ መንግስተ ሰማያት
አዳምንና እኛን ልጆቹን አሸጋግሮናል::

✥አባታችን አዳምና ልጆቹ ከሲዖል የወጡት በዕለተ ዐርብ በሠርክ ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ ዕለት እዲታሰብ ታዛለች::

✥ጌታችን ምርኮን ማርኮ: ጥጦስ መንገድ ጠራጊ ሆኖለት ወደ ገነት ሲያስገባቸው ለድንግል ማርያም አሳይቷታል:: እመ አምላክም በፍጹም ልቧ ደስ ተሰኝታለች:: አዳምና ልጆቹ እመቤታችንን ከላይ ሆነው እጅ ነስተዋታል:: እርሷ የድኅነታቸው ምክንያት ናትና::

✥አማናዊው ብርሃን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጨለማችንን በምሕረቱ ያብራልን::

✥ ክርስቶስም እኮ ስለ ሰው ኃጢአት አንድ ጊዜ ሞቶአል:: ኃጢአት የሌለበት ክርስቶስ ጻድቁ ስለ እኛ ሞተ:: ስለ ኃጢአታችን እኛን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ::
በሥጋ ሞተ: በመንፈስ ግን ሕያው ነው:: ነፍሳቸው ታስራ ወደ ነበረችበት ሔደ:: ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ነጻነትን ሰበከላቸው:: +"+ (1ዼጥ. 3:18)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
282 viewsMel፰ Yemamlak, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-08 12:19:17
ሰኞ = ጌታችን በሞትና ትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ሆና «ፀአተ ሲኦል ማዕዶት» ትባላለች፡፡ ዮሐ. 19-18 ሮሜ. 5-10-17 የዳግም ትንሣኤው ማግሥት ያለችው ግን ገበሬው፤ ወንዶቹ እርሻ ቁፋሮውን፣ ንግዱን፣ ተግባረ እዱን ሁሉ ሴቶቹ ወፍጮውን፣ ፈትሉን፣ ስፌቱን የሚጀምሩባት ዕለት ስለሆነች «እጅ ማሟሻ» ሰኞ ትባላለች፡፡
278 viewsMel፰ Yemamlak, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-02 00:27:51 Channel photo updated
21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-02 00:15:17
308 viewsMel፰ Yemamlak, 21:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ