ይህች ማን ናት??? ፡- 1.ፀጋን የተሞላች ከሴቶች ተለይታ የተባረከችና እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር የሆነ። * መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። የሉቃስ ወንጌል 1 : 28 2.በእግዚአብሔር ፊት ፀጋን ሞገስን ያገኘች። * መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። የሉቃስ ወንጌል 1 : 30 3.የሰላምታዋ ድምፅ ፅንስ በደስታ ያዘለለ። * ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ የሉቃስ ወንጌል 1 : 41 4.ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሏት ። * የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ የሉቃስ ወንጌል 1 : 48 5.ፍፁም ትሁት። * የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ የሉቃስ ወንጌል 1 : 48 6.ቅዱሳን ያከበሯት።* የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? የሉቃስ ወንጌል 1 : 43 7.ሰዎች በተጨነቁ ሰአት የምትማልድ። * የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። የዮሐንስ ወንጌል 2 : 3 8.ምልክት ፀሐይን የተጎናፀፈች አህዛብን ሁሉ በብረት በትር ይገዛ ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ የወለደች።* ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። የዮሐንስ ራእይ 12 : 1 * አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። የዮሐንስ ራእይ 12 : 5 9.ዘንዶው ያሳደዳት። * ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት። የዮሐንስ ራእይ 12 : 13 10.ዘንዶው በዘሯየተቆጣና ዘሯን ሊዋጋ የሄደ። * ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤ የዮሐንስ ራእይ 12 : 17 11.ውብ የሆነች።* ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥እንደ ኢየሩሳሌምም ያማርሽ ነሽ፤ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት ታስፈሪያለሽ። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 6 : 4 * ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና። መዝሙረ ዳዊት 45 : 11 12.የወርቅ ልብስ ተጎናፅፋ በእግዚአብሔር ቀኝ የምትቆም። የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። መዝሙረ ዳዊት 45 : 9 13.ንጉስ ዳዊት ልጄ ያላት።* ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ መዝሙረ ዳዊት 45 : 10 14.ልጆቿን ገዥ አድርጋ የምትሾም።* በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ። መዝሙረ ዳዊት 45 : 16 15.ተዘግቶ የሚኖረው የምስራቁ በር።* እግዚአብሔርም። ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል። ትንቢተ ሕዝቅኤል 44 : 2 16.የናቋት ሁሉ የሚሰግዱላት አማናዊት ፅዮን።* የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። ትንቢተ ኢሳይያስ 60 : 14 17.በድንግልና ፈጣሪዋን የወለደች ምልክት * ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7 : 14 18.እግዚአብሔር ያስቀረልን ዘር።* የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር። ትንቢተ ኢሳይያስ 1 : 9 19.ቅዱስ ጳውሎስ ንፅህት ድንግል ያላት። * በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11 : 2 20.ንገስታት የሚያመሰግንዋት።* ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት፤ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥ንግሥታትና ቍባቶችም አመሰገኑአት። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 6 : 9 21.ማን ናት???* ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት? መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 6 : 10። በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል። መዝሙረ ዳዊት 87 : 7። 393 viewsMel፰ Yemamlak, 04:23