Get Mystery Box with random crypto!

የወደደ ፍቅሩን ሸረሪትም ድሩን እንደማያስነካ እንዲዚያ ነኝ በቃ:: ወዶገባ ሆኖ ምርኮኛ ትካ | የኛ ግጥም ና ታሪክ

የወደደ ፍቅሩን
ሸረሪትም ድሩን
እንደማያስነካ
እንዲዚያ ነኝ በቃ::

ወዶገባ ሆኖ ምርኮኛ ትካዜው
እንዲሳካ ብሎ
እውነቱን ሸጦ ነው አፍቃሪ ለጊዜው።

“እሺ” ቢል ቢዋረድ ቢናቅም ቢዘበት
"ምንም አያመጣም" ብለሽ አትሳቂበት::

ለወናፍ ዐፍ ሁሉ ቢሆን መዘበቻው
የመጣበት ቀን ግን
በፍቅሩ ልክ ነው የአፍቃሪ ጥላቻው።