ለዚህ ነው 'ህይወትን' የማላምናት? ለዚህ ነው 'መኖር' 'የሰው ስም ብቻ ነው' የምለው:: ለዚ | የኛ ግጥም ና ታሪክ
ለዚህ ነው "ህይወትን" የማላምናት?
ለዚህ ነው "መኖር" "የሰው ስም ብቻ ነው" የምለው::
ለዚህ ነው "አለሁ" ማለት ነውር የሚመስለኝ::
ለዚህ ነው "ሳለን እንከባበር" እና " ሞትን እንቅደመው" የምለው::
እሳት ነው "ሞት" ያገኘውን ይበላል::
ጨለማ ነው "ሞት" ወደ-አለመተያየት ያስገባል::
"ሳይጨልምብን እንተያይ"
ኤልያስ ሽታኹን