Get Mystery Box with random crypto!

#እማሆይን ፍለጋ# #ለልባም ሴት# '...የሚነገሩ ንግርቶች፣ የሚጠቀሱ ጥቅሶች ፣የሚተረቱ ተረቶ | የኛ ግጥም ና ታሪክ

#እማሆይን ፍለጋ#

#ለልባም ሴት#

"...የሚነገሩ ንግርቶች፣ የሚጠቀሱ ጥቅሶች ፣የሚተረቱ ተረቶችም ልትሰሚ፣ልትዘከሪም ትችያለሽ። በመልክሽ፣በወዘናሽ ተለክቶ ስም ሊሰጥሽ ይችላል።
ቃላቶችሽን አክብሪያቸው ኑሪላቸው ለጥሩ አድማጭ አዊያቸው አልያም ዝምታን ምረጪ ለችግሮቿ መፍትሄ፣ለሀዘኗ ደስታን የምትፈጥር ከጥላቻ በላይ ፍቅርን ሰባኪ የሆነች ሴት ብልህ ነች።"
ይላሉ እማሆይ
"ወላጅ ቆንጥጦ ከሚያስተምረው
እድሜ ፈትኖ ሚያስተምረው ትምህርት እጅጉን የላቀ ነው።
የሰው ልጅ ምን ያህል ውድ እንደሆነ ዋጋውን የሚያውቀው አካባቢው ላይ እሱን አሳታፊ አሉባልታ ስለተቸረ ሳይሆን ማን እንደሆነ እራሱን ያወቀ ጊዜ ነው
አጥፍቶ እርሱ ስህተቱን እንዳልሆነ የተረዳ ወቅት ነው እራሱን ያወቀው ልጄ ከተጠበብሽ ምታውቀውን ስለሚመክሩሽ ስለምታከብሪያቸው ጆሮ ስጫቸው ጠቢብ ሴት ምክር ሳይሆን አዲስ ሀሳብን መቃረም ነው ሚበጃት።(ካላት ላይ ለመጨመር)
በስመአብ ስትዪ ማማተብን ከራስሽ እንደምትጀምሪው
መውደድን ከራስሽ ጀምሪ እራስ ወዳድ ሳይሆን እራስሽን የምትወጂ ሁኚ ያን ጊዜ ነው ሰው ሁሉ ጀርባውን ቢያዞር ቋሚ ምትሆኚው። ምታደርገውን ምታውቅ በራሷ ምትተማመን ልባም ከራሷ አልፋም ሰውን መካሪ እንደሆንሽ አውቃለው ሰዉ ጎድቶ በሸሸ ጊዜ በምድር ስብእና እና እውነት በሰማይ ፈጣሪ ብቻ መፅናኛ ሚሆነው ሁለቱን አጥብቀሽ ጨብጪ" ብለውኝ ዉሀ ተጎንጭተው ለቁርስ ለአቢ ከተሰራው የበሶ ጭብጦ ላይ ሁለቴ ቆነጠሩ
ወዲያው አቢ 'እማሆይ' እያለ ቁና ቁና ተንፍሶ ወደ ቤት ዘለቀ ለእማሆይ ተልኮ መመለሡ ነው።
አልቃሻ እማሆይ ከአምስት አመቱ ጀምሮ ያሳድጉት የነበረ የቀዬው ህዝብ 'እማሆይ አሁንም አድጎ ይሄ ልጅ መንሰቅሰቁን አልተወም እንደው ወንድ መሆኑንስ እንጃ' ሲሏት በስተርጅና ብስል የሆነችው እማሆይ "ሳሳድገው በሚያዝንበት፣በሚከፋበት ጊዜ አልቅሰው ይውጣልህ ብዬው ነው ይላሉ።"አቤት ጥበብ! አቤት መሠልጠን! ያለቀሰ ሁሉ ከማልቀሱ በፊት ላለማልቀስ እንደጠነከረ ሰው አላወቀ... አዎ ያልቅስ ሀዘኑ ከውስጡ ታምቆ ንፁህ ስብእናውን በበቀል እንዳይ ተካው እንባ አማላጅ ይሁን እንባ ሻሪ ይሁን።እንባ ድክመት አይደለም ሀዘንን መሻሪያ ዘዴ እንጂ።
በሉ እማሆይ እንዳይረፍድብኝ ልነሳ አየመጣው አዮታለሁ ብዬ እግራቸውን ስሜ አንዳች ነገር የቀረኝ ይመስል እፊታቸው ተገተርኩኝ አይኔን አይተው የገባቸው ይመስል "ደህና ሁኚ ቸር ይመልስሽ ብለው ሸኙኝ።" አሁንም ቅር እንደተሰኘ እያንገራገርኩ ከመኖሪያቸው ወጣሁ እማሆይ ጠቢብ ናቸው አንሰላስዬ ያሳነሱብኝ ምርቃት ቢበዛ ሀሴትን ፈጥሮ ያወጉኝን እንዳልዘነጋው መሆኑ ተገለፀልኝ.......

###እማሆይን እንፈልግ አልያም ልቦናችን ላይ እንገንባቸው...###

ደራሲ : ማህሌት ገድለ ሚካኤል (NiZ)