Get Mystery Box with random crypto!

'ቢጫ ሞት' ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ ~ ቢጫ አበባ ቆርጠ | የኛ ግጥም ና ታሪክ

"ቢጫ ሞት"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ቢጫ አበባ ቆርጠን አደይ ቀነጠስን
ለወረት ገላችን ተስፋ ነሠነሥን....

እንዲያው ይመስል በዓል
የውሸት ከነዓን
ሀሰት ወለደ ነዌ
የውሸት ነነዌ
ለሀሰት ወጋችን ለውሸት ማዕረግ
ስንት አደይ ስንት በግ?

እኛ
የማይጠብቀንን ወቅት እየጠበቅን
ተስፋን ሰበብ አርግን ስንቱን አረገፍን?
ጥያቄ?
ከስሩ ገንደሰን
ከግንዱ ቀንጠሰን ለኛ ተስፋ ያልነው
ለአደዩ ምንድነው?

ሞት::