Get Mystery Box with random crypto!

ኮንዶምን ለመጠጥ? —————————— በምስራቃዊ ህንድ የምትገኘው 'ዱርጋፑር' ከተማ ውስጥ የሚገኙ | ♒Orthopedic Surgery in Ethiopia ♒

ኮንዶምን ለመጠጥ?
——————————
በምስራቃዊ ህንድ የምትገኘው "ዱርጋፑር" ከተማ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ኮንዶሞችን በውሃ እየቀቀሉ ውኃውን የመጠጣት ልማድ እያዳበሩ በመምጣታቸው ምክንያት በከተማው ከፍተኛ የኮንዶም እጥረት እንደተከሠተ ተነግሯል።

ወጣቶቹ ይህንን የሚያደርጉት ኮንዶሙ መልካም ጠረን እንዲኖረው ተብሎ የሚጨመረው ኬሚካል ኮንዶሙ ከተሠራበት ፕላስቲክ ጋር አብሮ ሲቀቀል እና በሞቀው ውኃ ውስጥ ለብዙ ሠዓታት ተነክሮ ሲቆይ የአልኮልነት ባህሪ ወዳለው ሌላ አስካሪ ኬሚካልነት ስለሚቀየር  ፣ ወጣቶቹ ያንን ውኃ እየጠጡ አዲስ ሱስ ውስጥ ሊገቡ ችለዋል። በዚህም ምክንያት እዚያች ከተማ ውስጥ አዲስ የኮንዶም ምርት ገበያ ላይ እንደገባ ወዲያውኑ ተሽጦ ማለቅ ጀምሯል። የከተማው አስተዳደርም ጉዳዩን የደረሰበት ይሄንኑ ያልተለመደ የኮንዶም ፍላጎት መጨመርን ተከትሎ "ምን ተፈጥሮ ይሆን?" ብሎ ሲከታተል ነው።

"Durgapur Syndrome" loading ...