Get Mystery Box with random crypto!

ꔰ ሰኔ ፳፩ = ሰኔ ጎለጎታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳ | "መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

ꔰ ሰኔ ፳፩ = ሰኔ ጎለጎታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጎለጎታና ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
‹‹ሰኔ ጐልጐታ፤ ችግር የምትፈታ፤
ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህ ቀን ሰኔ ፳፩ ልጇን ወዳጇን ጎለጎታ በሚባል ቦታ ላይ እንበዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡
ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ)
ታላቅ በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት፡፡ ሐዋ 20፡28፡፡ በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ
ረጭተውታል፡፡ ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል፡፡
የብርሃን እናቱ ንግሥተ ሰማይ ወምድር
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ: በምልጃዋ: ከኃጥያትና ከበደል : ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ ትጠብቀን: አሜን።