Get Mystery Box with random crypto!

ሰኔ ፆም ነገ ሰኞ ይጀምራል ጾመ ሐዋርያት / የሴኔ ጾም / ቅዱሳን ሓዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወ | "መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

ሰኔ ፆም ነገ ሰኞ ይጀምራል
ጾመ ሐዋርያት / የሴኔ ጾም /
ቅዱሳን ሓዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም
ከመበተናቸው በፊት አገልግሎታቸው የተቃና እንዲሆን
የጾሙት ጾም ነው ፡፡
12 ናቸው ፡፡ ግን ዓለምን አዳረሷት ፡፡ መንፈስ ቅዱስን
ተቀብለናል ብለው ይበቃናል አላሉም ፡፡ ጾም ጨመሩበት ፡፡
መንገዳቸው ተቃና ፡ አውሬው ሰገደላቸው ፡ አንደበታቸው
እንደ ማር ጣፈጠ ፡፡
ዓልጫውን ዓለም በጨው / በስብከታቸው አጣፈጡት ፡፡
ክርስቲያን የአባቶቼ ጾም የኔም ነው ሲል ይህን ጾም ይጾማል
ፆሙን የበረከት ያድርግልን