Get Mystery Box with random crypto!

​​እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን! መልዐኩ ቅዱስ ዑ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!

መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤልና አገልግሎቱ በጥቂቱ

ዑራኤል የሚለው ስም "ዑር"እና ኤል ከሚለው ሁለት ቃላት የተመሰረተ ነው ። ትርጉሙም ብርሃነ ጌታ አምላክ ብርሃን ነው። ማለት ነው።

ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ መብረቅና ነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበቁ ነጓድጓድ ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። (መጽሐፈ ሄኖክ ፮፥፪)

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ እየመራ፤ ከእስራኤል ወደ ግብጽ ከዚያም ከእመቤታችን ጋር በሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው።

ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለበት ጊዜ፥ክቡር ደሙ በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን ነሳንስ የረጨው እሱ ነው።

ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ልቦና ያጠጣው፥ጥበብን ማስተዋልን የሰጠው የጠፉ መጽሓፍት በቃሉ አስታውሶ እንደገና ያጻፈው የረዳው መልአክ ነው።(ዕዝ፲፫፥፴፱)

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ትዕዛዝ ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ህይወት ስላጠጣቸው ነው።

በዓላቱም በዓመት 3ናቸው።
፩...ጥር። 22 በዓለ ሲመቱ፤
፪....መጋቢት 27 የጌታችንን ደም በዓለም የረጨበት፤
፫...ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ።

በጸሎቱ የተማጸነ ከእግዚአብሔር አምላክ በረከትን ፣ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ ጠባቂ ና የዋህ መልአክ ነው።በተለይም ህጻናትን የሚጠብቅ የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ ፥ኃጢአተኞች ካሉበት ቦታ እኔን ላከኝ እያለ አምላኩን የሚማጸን አዛኝ የዋህ መልአክ ነው።

ይህ አለም በአማላጅነቱ አምኖ በእምነት ጸበሉን ቢጠጣ ፥ዝክሩንም ቢዘክር ከክፉ በሽታው እንደሚድን፤ እንደሚፈውሰው ቃል ኪዳን ተሰጥቶታል ።

ቅዱሳን መላዕክት እግዚአብሔርን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራሉ ከመከራም ያድኑዋቸዋል።(መዝ ፴፫÷፯) የአባታችን የጠባቂያችን የአማላጃችን የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል ቃል ኪዳን አይለየን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur