Get Mystery Box with random crypto!

#ኦ_ሚካኤል ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/ ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል ዘንዶው | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ኦ_ሚካኤል

ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/
ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል

ዘንዶው ጠላታችን ከፊታችን ቆሟል
ከባህር ሊጥለን አድፍጦ ያደባል
የመላዕክት አለቃ እርዳን በፀሎትህ
ጥበቃህ አይራቀን በቀን በሌሊት/2/

ክርስትና ኑሮ እጅጉን ከብዶናል
የጌታን ውለታ ፍቅሩን ዘንግተናል
አፅናኙ መልዐክ ከፊታችን ቅደም
በመንገድህ ምራን እንድንሆን ሰላም/2/

የጌታ ባለሟል የህዝብ እረኛ
ባህሩን አሻግረን ቅረበን ወደ እኛ
ከጌታህ አማልደን መልዐከ ራማ
የልጆችህን ቃል ድምፃችንን ስማ

በሚያስፈራው ዘመን ሰላም በሌለበት
ባስጨናቂው ጊዜ ፍቅር በጠፋበት
የፍቅርን ወንጌል ቃሉንም ስበከን
ሚካኤል ተራዳን ድረስም አፅናናን

ዘ/ዲ ሱራፌል ስዩም
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur