Get Mystery Box with random crypto!

'የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕመም ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው::' የሮም ካቶ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕመም ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው::" የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን

የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአጋርነት ደብዳቤ በፖፑ የክርስቲያን አንድነት ፕሬዝደንት በኩል ላከች::

ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮህ የፖፕ ፍራንሲስ የክርስቲያኖች አንድነት ፕሬዝዳንት (President Pontifical Council for Prompting Christian Unity) እንደገለጹት "በተፈጠረው ችግር እና ሁኔታ ጥልቅ ሐዘን የተሰማን ሲሆን ለቅዱስ ሲኖዶስ ያለንን አጋርነት በመግለጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረትን በሙሉ እንደግፋለን" ብለዋል::

በመልእክታቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በላከው የመጀመሪያ መልእክት “አንድም ብልት ቢሰቃይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።” 1ኛ ቆሮንጦስ 12፥26 ያለውን ጠቅሰው ሕመሟ ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው ሲሉ በአጽንዖት ገልጸዋል።

በመጨረሻም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት እናት በምልጃዋ እጅግ የተከበረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷና ደህንነቷ እንዲጠበቅ ታድርግልን ብለዋል።