Get Mystery Box with random crypto!

'ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ' በሚል ርዕስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ/ም | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

"ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ" በሚል ርዕስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ/ም የመንግስት ኮምዩኒኬሽን የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ።

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ እንዲሁም በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ ፲፱ ንኡስ አንቀጽ ፫ በተደነገገው መሠረት ጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የሃይማኖት፣ የቀኖና እና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ሕገ ወጥ ሲመተ ጵጵስና እና መፈንቅለ ሲኖዶስ ሙከራ በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ አካል በኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጡ ውሳኔዎች እና መልእክቶች ተከታታይ መድረኮች በማዘጋጀት ስለ ተፈጠረው የሃገራችን ሕግ እና የሕገ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በቂ ግንዛቤ ሕዝባችን እንዲያገኝ በተደጋጋሚ ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት አማካኝነት መግለጫ እና ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ይሁንና "በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ" በሚል ርእስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ፤ መግለጫው ያስቀመጣቸው ነጥቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ክብር፤ ታሪክ፤ እና እውነታ ቸል በማለት በጉዳዩ ላይ የተሟላ መረጃ የሌላቸው ወገኖች የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዙ የሚያስችል መግለጫ በመኾኑ በመግለጫው አንኳር ነጥቦች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።