Get Mystery Box with random crypto!

#ተው_ዓለም_ተመለስ ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ በቁ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ተው_ዓለም_ተመለስ

ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
በቁጣ መዓቱ ይቀጣሃል ጌታ ይቀጣሃል ጌታ

ትውልዱ ተመታ በታላቅ በሽታ /፪/
ኧረ በልክ ይሁን ጭፈራና ደስታ /፪/
በማዕበል በጎርፍ እያየህ ሲቀጣ/፪/
አሁንም ተመለስ የከፋ ሳይመጣ /፪/
#አዝ
ነነዌን ሊያጠፋ የወረደው እሣት /፪/
አንተን እዳይመታህ ተነሳ ለጸሎት/፪/
ዓለም ብትሰጥኽ አንተ እድትተጋ /፪/
ሀልወተ እግዚአብሔር እንደምን ይዘንጋ
#አዝ
ችግር ለበዛበት እጅግ ለታወከው/፪/
አምላክ መሐሪ ነው ለተንበረከከው/፪/
የዓለም መድሐኒት የዓለሙን ቤዛ /፪/
ጠይቀው ምሕረትን ሠው ሆይ ልብ ግዛ
#አዝ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
በቁጣ መዓቱ ይቀጥሃል ጌታ ይቀጣሃል ጌታ።

ሊቀ መዘምራን
ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur