Get Mystery Box with random crypto!

#መከራው_ክርስትናዬን_አጣፈጠው ✞ መከራው ክርስትናዬን አጣፈጠው ስደቱ ማህተቤን አጠበቀው በሞት | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#መከራው_ክርስትናዬን_አጣፈጠው ✞

መከራው ክርስትናዬን አጣፈጠው
ስደቱ ማህተቤን አጠበቀው
በሞት መንደር በሀዘን ውስጥ በመከራ
አየውት እግዚአብሔርን ከኔ ጋራ

ክርስትያን ተብለን በክርስቶስ ስም የተጠራነው
በጥልቁ ውስጥም በእግዚአብሔር እንድናምን ነው
ለጥቂት ግዜ ቢበረታብን ስደት ሀዘኑ
አምላክ ግን መውጫ ያዘጋጃል በዚህ ተፅናኑ
#አዝ
በስደት ሳለን ካፋችን ቢደርቅ የፅዮን ዜማ
ከወንዙ አጠገብ ቁጭ ብለን ሰለን ድምፁን ሳንሰማ
በእግዚአብሔር ጊዜ ከባቢሎን ምድር እንለቃለን
መሰንቆአችንን ከአርያም ዛፍ ላይ እናወርዳለን
#አዝ
ደካሞች ሲሉን በስሙ ያን ጊዜ እንበረታለን
ድሆች ስንባል ባለጠጎች እናደርጋለን
በምድር ቅዱስ ህዝብ አድርጎ ለእርሱ ለየን
ጨለማው አልፎ በቸርነቱ ብርሀን አሳየን
#አዝ
ከፀጋ በላይ እንዳንፈተን ይከልለናል
በቁስላችን ላይ የፈውስን ዘይት ያፈስልናል
በጊዜም ቢሆን ያለ ጊዜውም በእርሱ እንፅና
እንኳን ስደቱን ሞቱን ሊገታው ይችላልና

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur