Get Mystery Box with random crypto!

በሻሸመኔ እና በመላው ምዕራብ አርሲ የምትገኙ ጠንካራ ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በሙሉ ይህንን ከዘመ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በሻሸመኔ እና በመላው ምዕራብ አርሲ የምትገኙ ጠንካራ ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በሙሉ ይህንን ከዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ያልተናነሰ ዘመን በጠንካራ መሠረት ላይ በታነፀው የሃይማኖታችሁ ጥንካሬ በጸሎት ፣ በጾም እና በፍፁም ክርስቲያናዊ ጥንካሬ ራሳችሁን ፣ ቤተ ክርስቲያናችሁን እና ሀገራችሁን እንድጠብቁ ሲሉም ጠይቀዋል።

በመሆኑም ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል በማስተዋል የፌደራል መንግስትና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወገንተኝነታቸውን በማቆም እግዚአብሔር ፍርድ ከመስጠቱ በፊት ንስሐ በመግባት በግፍ የሚፈሰውን የንፁሐን ኦርቶዶክሳውያንን ደም እንዲያስቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል