2022-06-23 20:17:09
ወላዲተ አምላክ ስለመሆኗ
ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እናምናለን ። ይኸውም ወልደ አብ ኢየሱስ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ በሥጋ ወልዳዋለችና ። ለዚህ ማስረጃ የሚሆኑንን ጥቅሶች እንመልከት ምክንያቱም ድንግል ማርያምን እንደ ማህደር ተጠቀመባት እንጂ ወላዲተ አምላክ አትባልም ብለው የሚያምኑ ስላሉ ፦ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች " ትን ኢሳ 7:14 ይህ ቃል የሚወለደው ሕፃን አማኑኤል ተብሎ ይጠራል የወለደቺውም ድንግል ናት ካልን ከቃሉ ከፍ ብሎ እንዲህ ይለናል፦
"እርሱም አለ እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ ስሙ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን አምላኬ ደግሞ የምታደክሙ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣቹዋል " ኢሳ 7:13 ይህን ቃል ልናጤነው ይገባል የእስራኤል ቤት ብቻ ሳይሆን አለሙ ሁሉ ለመትረፍ በሰው ድካም አልሆነም ። አሁን ግን አምላክ ሊደክም የኛን መከራ ተሸክሞ ሊያድነን መጣ ። እርሱም #ምልክት ሰጠን #ምልክታችንም ድንግል ማርያም ነች አምላኬን የምታደክሙ ያለው ደግሞ ከድንግል የሚወለደው አምላክ መሆኑን ለማመልከት ነው
እናቱንም ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላ ጥቅስ እንይ ፦ "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል "ኢሳ 9:6 ሕፃን ተወልዶልናል እርሱ ደግሞ ኃያል አምላክ ነው ። ስለዚህ የወለደቺው ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ እንላታለን ። ይኸውም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በ#ተዋህዶ ከብሮ ተወልዷልና ። ሌላም ጥቅስ እንጨምር ፦ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል " ሉቃ 1:43 አስተውሉ ስራው የመንፈስ ቅዱስ ነው ኤልሳቤጥ አክስት መሆኗን እንጂ ድንግል ማርያም የጌታ እናት ትሁን አትሁን የምታውቀው ነገር የለም
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልታ ስለነበር የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል ስትል የጠየቀቺው ስለዚ ነው ። መንፈስ ቅዱስን የተሞላ ድንግልን ያውቃታል ፣ ያከብራታል ፣ ያመሰግናታል እርሱ ጌታ ነውና ወላዲተ እግዚዕ እርሷ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላም እንይ ፦ "ቃል ሥጋ ሆነ ፀጋንና ክብርን ተመልቶ በኛ አደረ " ዮሐ 1:14 ያ ቃል ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐ 1:1 ላይ "ቃል እግዚአብሔር ነው " ስለዚህ የተወለደው የኛን ሥጋ የተዋሀደውን ክርስቶስ ኢየሱስን በሥጋ የወለደቺው ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ። ሌላ ፦ "ነገር ግን የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ " ገላ 4:4 ሴቲቱ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ነች
በአጭሩ ፦
እርሱ አምላክ ስለሆነ እርሷም የአምላክ እናት ትባላለች
እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር እናት ትባላለች
እርሱ ጌታ ስለሆነ እርሷም የጌታ እናት ትባላለች
እርሱ ብርሃን ስለሆነ እርሷም የብርሃን እናት /እመብርሃን/ ትባላለች። ጌታ አምላክ እናቱን ማደሪያው ስላደረጋት ከፈጣሪ በታች በሰማይና በምድር ከከበሩ ሁሉ የከበረች ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ናት ስለዚህም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት እያሏት እያመሰገንዋት ይኖራሉ ስሟንም እየጠሩ በደስታ እየዘለሉ ይዘምራሉ ሉቃ 1:39-55 ልጇ አምላክ ነው እርሷ እናቱም ወላዲተ አምላክ ናት
@ortodoxian
@ortodoxian
102 views17:17