Get Mystery Box with random crypto!

+++ የመነኩሴው ፈሊጥ +++ መጾም ያቃተውን ሰው ጹም፣ መመጽወት የተሳነውን መጽውት | ✝️ቅዱስ ኤልሻዳይ✝️አምላክ እልመክኑን✝️

+++ የመነኩሴው ፈሊጥ +++


መጾም ያቃተውን ሰው ጹም፣ መመጽወት የተሳነውን መጽውት፣ መራመድ የማይችለውን ሩጥ የሚሉ መካሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ መራመድ የማይችል እንዴት መሮጥ እንዳለበት ከማሳየት ይልቅ ቀንበር ማክበድ ጠባያችን ሆኗል፡፡ ይህ የሚያሳየው ቃሉ እንጂ ተግባሩ የተለየን መሆኑን ነው፡፡ በተግባር መግለጥ ብንችል ኖሮ፣ ማገዝ ቢያቅተን እናሯሩጠውና ሰውነቱ ሞቆ ተጋድሎ ሲጀምር እናፈገፍግ ነበር፡፡ እኛ ግን ልምድ የሌለውን ሁሉ ተሸከም ማለት ይቀለናል፡፡

ከባለ ግመሉ ከአባ ቆሪር ምክር ለመመጽወት የሄደ ክርስቲያን ግመሉ ከሚችለው በላይ ስለጫነው አንተ አቅም አጥተህ ምክር ለመቀበል መጥተህ ሳለ ግመሉን ካለ አቅሙ ለምን ጫንከው ተብሏል፡፡


ከዐቅማቸው በላይ ተሸክመው የከበዳቸውን ሰዎች በማገዝ ሸክሙ ሳይከብዳቸው፣ ከክርስቲያናዊ ተጋድሎ ሳያፈገፍጉ በእምነት እንዲኖሩ ማገዝ ከዘመናችን የሃይማኖት ሰዎች የሚጠበቅ መሆኑን ለማስታወስ የአባ ዳንኤልን ፈሊጥ በአብነት እጠቅሰዋለሁ፡፡

አንድ አባ ዳንኤል የሚባል መነኩሴ ነበር፡፡ የደከመ ባገኝ አግዛለሁ እያለ በጨረቃ ከበዓቱ ወጥቶ ገዳማውያን በሚገኙበት በረሓ ይዞር ነበር፡፡

በአንድ ወቅት የማትሠራው ኃጢአት ያልነበር፣ ከጽድቅ ተግባር የማትተዋወቅ ሴት አገኘ፡፡ አባ ዳንኤልም ሴቲቱን ወደ ሴቶች ገዳም ወስዶ ልብላ ካለች ትብላ፣ ልተኛ ካለች ትተኛ፣ የፈቀደችውን ሁሉ ታድርግ፣ የገዳሙ ሕግ አይፈቅድም በማለት ቀንበር አንዳታከብዱባት ብሎ ለእመምኔቷ አስረክቧት ሔደ፡፡

እመምኔቷም እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ ሴቲቱ በፈለገች ጊዜ ትበላለች፣ ስትፈልግ ትተኛለች፡፡ ያሰኛትን ታደርጋለች፡፡ ግን ደስታ የላትም፤ አብረዋት የሚኖሩት መነኮሳት ቤተ ክርስቲያን አድረው፣ በሥራ ተጠምደው ሲኖሩ ተመለከተች፡፡ እሷ በልታ ይርባታል፡፡ እነሱ ሳይበሉ አይራቡም፣ እሷ ተኝታ ይደክማታል፣ እነሱ ቆመው ውለው፣ ቆመው አድረው ድካም አያውቁም፡፡ ቀስ በቀስ መገረም፣ ከዚያም በሕይወታቸው መቅናት ጀመረች፡፡


ምግብ ሲያቀርቡላት እስከ ሦስት ሰዓት ልቆይ ማለት ጸሎት አድርጋ መብላት ተለማመደች፡፡ ቆየችና እስከ ስድስት ልቆይ አለቻቸው ከዚያም እስከ ዘጠኝ፣ ከዚያም በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ መመገብ ጀመረች፡፡ ከዚያም ከሳምንት አንድ ቀን ብቻ መቅመስ በመጨረሻም በዓቷን ዘግታ በሦስት ሳምንትም፣ በወርም በሕይወት ለመቆየት ያህል መቅመስ ደረሰች እንዲህ ድክመታችን ታግሠው ለክብር የሚያበቁን ባለ ፈሊጥ መምህራን ማግኘት ለዚህ ዘመን እንዛዝላ ተሸካሚ ከዕንቊ የበለጠ ስጦታ ነው እላለሁ፡፡

✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖