Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙር 22 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹² ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ፤ ¹³ እንደ ነ | የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮችና ትምህርቶች

መዝሙር 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

¹² ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ፤

¹³ እንደ ነጣቂና እንደሚጮኽ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።

¹⁴ እንደ ውኃ ፈሰስሁ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ።

¹⁵ ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጕሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አሸዋ አወረድኸኝ።

¹⁶ ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።

¹⁷ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።

¹⁸ ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።


https://t.me/Ortodox_Tewaahdo