Get Mystery Box with random crypto!

ንግስት ሆይ ቅድስት ሆይ ለሁሉ ደስታ የሚሆን የልደትሽን ነገር ሳስብ... መሰረቶቿ በተቀደ | የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ

ንግስት ሆይ ቅድስት ሆይ

ለሁሉ ደስታ የሚሆን የልደትሽን ነገር ሳስብ...

መሰረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ላይ ነው ፤ የሚለውን የአባትሽን የዳዊትን መዝሙር አስታውሳለሁ ፤ ቀደምት አባቶችሽ ደጋግ ፣ ጽኑና ብርቱ ፣ ከምድር ከፍ ያሉ የመሆናቸውን ነገር አስተውላለሁ።

መካን ከሚሆኑ ፥ ከአባትሽ ከኢያቄምና ከእናትሽ ከ ሃና የመወለድሽን ፤ ለወላጆችሽ እንዲሁም ለዓለም ሁሉ ደስታ የመሆንሽን ነገር አስባለሁ። ይህም ልምላሜ ለማይገኝብኝ ፤ ፍሬ ምግባር ፥ ፍሬ ሃይማኖት ለማይገኝብኝ ፤ መካን ለሆንኩ ለእኔ ለልጅሽ ተስፋ ይሆነኛል።

ምንም እንኳን ዛሬ አዕምሮዬ ይቡስ ፥ ልቦናዬም የበጎነት ፍሬ የማይገኝበት መካን ቢሆንም  ልክ እንደ ቴክታና ጴጥሪቃ ፥ ሃናና ኢያቄም ሁሉ የደጋግ ሃሳቦችና የመልካም ምግባር ፍሬዎች መገኛ ይሆንልኝ ይሆናል!

የጌታዬ ፍቅር ፣ የእመቤቴ የእናትነት ፍቅር በልቤ ውስጥ ይታተም ፣ ይፀነስና ይወለድልኝ ይሆናል። ይህም ለእኔና በዙርያዬ ላሉት ሁሉ ታላቅ ደስታና የምስራች ይሆን ይሆናል የሚል ብርቱ ተስፋን እይዛለሁ!
እናቴ ሆይ ይሁንልኝ ፥ ይደረግልኝ!
መካንነት ይብቃኝ ፥ አሁን ይደረግልኝ!!!

ቃል ለማይገልጣት ንጹሕና የፍጥረት ኹሉ ጌጥ ለኾነችው ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል እንኳን አደረሳችሁ።
እናቴ ልደትሽ ልደታችን ነው!!!