Get Mystery Box with random crypto!

“ወንድሞቼ ሆይ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደሙሉ ደስታ ቁጠሩት” ያዕቆብ 1፥2 የ2015 ዓ.ም | የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ

“ወንድሞቼ ሆይ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደሙሉ ደስታ ቁጠሩት” ያዕቆብ 1፥2
የ2015 ዓ.ም የነነዌ ጾም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በገጠማት ችግር ምክንያት ከእስከዛሬው በተለየ መልኩ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ ከቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምህረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ በአስተላለፈው ጥሪ መሠረት እየተጾመ ይገኛል፡፡
በዚህም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ምእመኑ የቅዱስ ሲኖዶስን ጥሪ በመቀበል ወደ እግዚአብሔር ጸሎተ ምሕላን ሲያቀርብ ተመልክተናል፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ልመናችንን ሰምቶ ከሚመጣው መዓት በቸርነቱ እንዲታደገን የጸሎት ትኩረት የሚያሳጡንን ሁሉ በመተውና ዓላማውን በመረዳት በጸሎት እንበርታ፡፡ ሐዋርያው ያዕቆብ (1፥2) “ወንድሞቼ ሆይ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደሙሉ ደስታ ቁጠሩት” በማለት እንደገለጸልን እኛም የሚያጋጥሙንን ችግሮች በዝምታ ብቻ በማለፍ መከራን በመቀበል እንድንጸና ይሁን እንላለን፡፡
የጥር 29 ቀን የጾመ ነነዌ ጸሎተ ምሕላ ፎቶ የተወሰኑትን ይመልከቱ፡፡