ሰበር ዜና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመንግስት የተለያዩ ተቋማትና በተወገዙት | የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ
ሰበር ዜና
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመንግስት የተለያዩ ተቋማትና በተወገዙት የቀድሞ ሶስት "ጳጳሳትና የተሾሙት 25 ጳጳሳትን" ከሰሰች
ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው
√ የቤትክርስቲያንን ክብርና ስም በመንካት
√ በሕይወት የመኖር፣ የመዘዋወር እና የማምለክ መብትን በመንካት
√ መንግሥት ሁሉን ሰው በእኩል ሕጋዊ ጥበቃ እና በእኩልነት የማየት ሕገመንግሥታዊ ኀላፊነትን ባለመወጣት
√ የቤተክህነት ንብረት ሲዘረፍ እርምጃ ባለመውሰድ
√ ጳጳሳትን እና የቤተክህነት ሕጋዊ መዋቅር ውስጥ ያሉትን በማፈን፣ በማሰርና በማስፈራራት
√ የመንግሥት ሚዲያ በሕዝብ ሀብት እየተዳደረ የቤተክርስቲያኗን መግለጫ እና የደረሰባትን የሕግ ጥሰት ባለመዘገብ ህገመንግሥታዊ ኀላፊነትን ባለመወጣት
√ አቶ ኀይለ ሚካኤል ታደሰ የተባሉ የሕገ ወጦቹ ቃል አቀባይ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ፀብ አጫሪ ቅስቀሳ በማድረጋቸው ተከሰዋል።
ክሱ ሰኞ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስምንት ሰዓት ይሰማል።