Get Mystery Box with random crypto!

'★መንግሥት በአስቸኳይ ይህንን የርኩሰት ፊልም ያስቁም!' ★ ክርስቲያኖች ተጠንቀቁ!! ' ፍልሰት | ORACLE OF CHRIST

"★መንግሥት በአስቸኳይ ይህንን የርኩሰት ፊልም ያስቁም!"

★ ክርስቲያኖች ተጠንቀቁ!! " ፍልሰት" በሚል ርዕስ በቃና ቲቪ የሚተላለፈውን የሴት ሰዶማውያን /ሌዝብያን / ፊልም ፈጽሞ እንዳታዩ። ★ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ለገንዘብ የሚስገበገቡ፣የራሳቸውን ጥቅም እንጂ በትውልድ ሕይወት ላይ የሚያመጣውን መጥፎ ተጽኅኖ የማያገናዝቡ ስግብግብ ግለሰቦች ያገኙትን የውጪ ፊልም ሁሉ በገንዘባቸው እያስተረጎሙ ትውልድን እያረከሱ ሃገርን እያቆሸሹ ይገኛሉ።

ይህ "ፍልሰት" የሚል የማታለያ ትርጉም የተሰጠው ፊልም "Orfaos da Terra" ከሚል የፓርቹጋል ቋንቋ የተወረሰ ሲሆን የፊልሙ ዋና ዓላማ በስደትና በፍቅር ስም የሴት ሰዶማዊነትን /ሌዝቢያዊነትን/ በትውልድ ልብ ውስጥ ለማስገባትና ወጣቶችን በረከሰ ተግባር ለማጥመድ በምሥጢር ታቅዶ የተሰራ ፊልም ነው። ፊልሙ እጅግ በረቀቀ ዘዴ ወጣቶችን በመሳብ ልባቸውን እያንጠለጠለ የአዕምሮ እጥበት/Brain wash/ በማድረግ ሴት ከሴት ጋር በዝሙት መጨመላለቅን እንደ ዘመናዊነትና እንደ ሥልጣኔ ለማሳየት የተዘጋጀ አጋንንታዊ ፊልም ነው።

እንዳይታወቅባቸው ግን በጦርነት ምክንያት የሚፈጠር ስደት አስመስለው ነው ያቀረቡት። ፊልሙ በማር የተለወሰ መርዝ ነው።... ስለዚህም ይህ" ፍልሰት " በሚል ርዕስ በተከታታይ ለሕዝብ በይፋ በቃና ቲቪ የሚተላለፍ ነውረኛ ፊልም በአስቸኳይ መቆም አለበት።

@oraclekb