Get Mystery Box with random crypto!

የምናመልከው እየሱስ እግዚአብሄር ሁሉን ነገር የፈጠረበት፣መጀመርያውም መጨረሻውም የሆነ፣እግዚአብሄር | ORACLE OF CHRIST

የምናመልከው እየሱስ እግዚአብሄር ሁሉን ነገር የፈጠረበት፣መጀመርያውም መጨረሻውም የሆነ፣እግዚአብሄር የተንፀባረቀበት፣እግዚአብሄር የተናገረበት፣በውስጣችን የተሰወረው የእግዚአብሄር ሚስጥር፣በሰማይ ያለው ብቸኛ አማላጃችን፣እግዚአብሄር የሀጥያት ይቅርታ የሚያደርግበት ብቸኛው መንገድ፣እግዚአብሄር አብ የሚታወቅበት ብቸኛው መንገድ፣ፅድቅም ጥበብም ቅድስናም ቤዛነትም ከእግዚአብሄር ዘንድ የሚገኝበት መንገድ፣እግዚአብሄር ፍቅሩን የገለጠበት፣የእግዚአብሄር አንድያ ልጅ፣እርሱን በማመን የሀጥያት ይቅርታ የሚያስገኝ፣የእግዚአብሄር ውዱ ስጦታ፣የዘለአለም ህይወት ያገኘንበት መንገድ፣በኛና በእግዚአብሄር ያለው መሀከለኛ፣ፀሎታችን ተሰሚነት የሚያገኝበት መንገድ፣ወደ እግዚአብሄር የሚያደርሰን መንገድ፣ከዘለአለም ፍርድ የሚያድነን መንገድ፣ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያስገባን በር፣እርሱን በማመናችን መንፈስ ቅዱስን ያገኘንበት መንገድ፣እግዚአብሄርን የምናመልክበት፣የነፍስ እረፍት የሰጠን፣የነፍሳችን እረኛ፣መዳን ያገኘንበት መንገድ፣የቤተክርስቲያን ራስ፣በሞቱ ከእግዚአብሄር ጋር ያስታረቀን፣የእግዚአብሄር ልጆች ያረገን፣በእግዚአብሄር ዘንድ ያለ ጠበቃችን፣ከሀጥያት ያነፃን፣የመለኮት ሙላት የሚኖርበት፣የእግዚአብሄር የተስፋ ቃሎች ፍፃሜ ያገኙበት፣የስብከታችን ርእስ፣እግዚአብሄር ስሙት ያለው አካል፣ከአዳም ጀምሮ ቅዱሳን ያመኑት፣የቤተክርስቲያን መስራችና መሰረት፣በእግዚአብሄር ቀኝ ያለ ሊቀ ካህናችን፣ስለ ስሙ መነቀፍ ከሁሉ የሚበልጥ ባለጠግነት የሆነለት፣የእግዚአብሄር ጥበብና የእግዚአብሄር ቃል፣ያለ እርሱ ምንም ማድረግ የማይቻል፣ወደ እግዚአብሄር ቤት መግቢያው በር፣የጥበብና የእውቀት መዝገብ ያለው፣የሰይጣንን ራስ የሚቀጠቅጠው የሴቲቱ ዘር፣ታላቁ አምላካችን፣መድሀኒታችን፣አዳኛችን፣የምንጠብቀው የተባረከው ተስፋችን እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ.....


እየሱስ ማነው ከሚል መፅሀፍ የተወሰደ

@oracleKB