Get Mystery Box with random crypto!

አፀዳድተን እንጠብቀው!! ባለቤቴና እኔ ቤታችን እንግዳ የጋበዝን ለታ አይ የሽር ጉዱ ብዛት! | ORACLE OF CHRIST

አፀዳድተን እንጠብቀው!!

ባለቤቴና እኔ ቤታችን እንግዳ የጋበዝን ለታ አይ የሽር ጉዱ ብዛት!

ማብሰያ ቤቱ ይፀዳል
መታጠቢያ ቤቱ ራሱ ይታጠባል
ወለሉ ልቡ እስኪጠፋ ይወለወላል
አልጋዎቹ ዘንጠው ይነጠፋሉ
ወንበር ጠረቤዛው በአግባቡ ስፍራውን ይዞ ይቀመጣል
መብራቶቹ ፍዋ ብለው በያሉበት ድምቀት ይጨምራሉ
መልካም ጠረን አየሩ ላይ ተሽ ተሽ ይደረግበታል
ምግቡ ደግሞ ባማረ ሁኔታ ተሰናድቶ እነሆ እያለ ይጠብቃል!

በማንኛውም መንገድ የእንግዳችንን ምቾት የሚነሳ አንዳች ነገር እንዳይኖር ልባችን ውልቅ እስኪል ድረስ ተዘጋጅተን እንጠብቃለን!

ተጋባዡ በቤታችን የሚኖረው ቆይታ ፍፁም ደስታን የሚፈጥርለት እንዲሆን እንጂ ምንም ዓይነት ቅሬታ እንዳይሰማው ጠብ እርግፍ ብለን ሁሉን አሰማምረን ስናበቃ በፈገግታ ውጭ ውጭውን እያየን እንጠብቀዋለን!

ታዲያ...........

ኢየሱስዬ እኮ ከየትኛውም ወዳጃችን
የሚበልጥ ተናፋቂ እንግዳችን ነው!!
ሃሌሉያ!!!

ልባችንን አፀዳድተን እንጠብቀዋ!!!
"እኛ ቤቱ ነን" እንዲል መፅሐፉ!

አሁን መንፈስ ቅዱስን ብንጠይቀው የፅዳቱን ዓይነትና መጠን ሰፈሩን ከነቀበሌው ከነቤት ቁጥሩ ይኸውልህ/ ይኸውልሽ / ያቺኛዋ/ ይሄኛው / ያኛው አየኸው አይደል? እያለ ዘርዝሮ አብጠርጥሮ ይነግረናል እኮ!

እኛ እሺ እንበል እንጂ መንፈስ ቅዱስማ ሁሌም ዝግጁ ነው!

ዛሬም መንፈስ ቅዱስ የአገልጋዮን የጳውሎስን አንደበት ተውሶ እንዲህ ይለናል!

"በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና: እንደ ንፅሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና"

2ኛ ቆሮ 11:2

ቸር ቆዮልኝ

ዘማሪ ዶ/ር ለዓለም ጥላሁን
Join us
Join us
@oracleKB