Get Mystery Box with random crypto!

አምላኬ ሆይ ልቤን ካሸፈተው ከሐጥያቱ ባህር ወድቄ እንዳልቀር ከትቢያ ከአፈር በል አቅናኝና አንፃ | 💙

አምላኬ ሆይ

ልቤን ካሸፈተው ከሐጥያቱ ባህር
ወድቄ እንዳልቀር ከትቢያ ከአፈር
በል አቅናኝና አንፃኝ ከእድፌ
እንዳመሰግንህ ከሰው ተሰልፌ
ደሞ
እንደ ሰው ሁሉ የለኝ ማነጥፍልህ
ሆሳዕና እያልኩ አንዳች ማደርግልህ
ግና
ለአንተ መድሀኒቴ ለፈጠርከኝ ጌታ
አንዳች ባላገኝ ፍፁም የምሰጥህ
ይኸው ልቤን አነጠፍኩ በፍፁም ደስታ
እናም መዳኒቴ ሆይ
በል ግባ ከእልፍኜ
ሆሳህና
ሆሳህና
ሆሳህና
እያልኩ እንዳመሰግንህ ከህፃናቱ ጋር ሆኜ ።

እንኳን አደረሳችሁ ።

ልጅ ዳን የእናቱ ልጅ