2022-08-22 12:59:32
እንዲሆን ሞገስ ዘውዴ የአንገት . (1) .
ሁሌ ቃላህ ነውና የእግሬ መብራት
መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት (2x)
አቤቱ እንዳልበድልህ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
መንገድም እንዲነጻልኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
በትዕዛዝህ መንገድ እንድሮጥ
ተንሸራትቼም እንዳልገባ ማጥ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ስንፍናን ተግቼ ኃጢአትን ሳላምጥ
ሕይወቴ በድንገት እንዳያመልጥ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ስትተትን እንዳስተውላት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
እንድሰወር ከስውር ኃጢአት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ከጓደኞቼ ጋር በሳቅ ጨዋታ
መስመር እንዳላልፍ እንዳልረሳ ጌታ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
የድፍረት ኃጢአት ጠፍሮ እንዳይዘኝ
ቃልህ ፍርሃት ሁልጊዜ እንዲያዘኝ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ቃልህ ይሁን ትዝታዬ ቃልህ ይሁን (2x)
መፅናናት ሲያስፈልገኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
መከራው ሲያሳድደኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ከጠላቴ ዛቻ ከምክሩ እንዳልፈራ
ልቤ እንዲጠበቅ በምክር እንድመራ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
የኃጥአን ገመዶች ሲተበተቡብኝ
አለቆች ተቀምጠው ሲያሙኝ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
በአመፀኞች እንዳልቀና ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
የግፍ እንጀራ እንዳልበላ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
. (2) . ኑሬ ቤቴን ለመሙላት
በከንፈሬ . (3) .
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
እግሬ እንዲከለከል ከክፋት ጐዳና
በፈተና ሁሉ እምነቴ እንዲፀና
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ቃልህ ይሁን ትዝታዬ ቃልህ ይሁን (2x)
ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ
እንዲሆን ሞገስ ዘውዴ የአንገት . (1) .
ሁሌ ቃላህ ነውና የእግሬ መብራት
መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት (2x)
ቤቴሌሄም ተዘራ #4
144 viewsBiniam Solomon, 09:59