Get Mystery Box with random crypto!

መስታወት..... ብዙዎቻችን መንፈሳዊ ዓለም የማይነካና የማይጨበጥ ይመስለናል ልንረዳ የሚገባው | የእግዚአብሔር ፀጋ- THE GRACE OF GOD👑

መስታወት.....

ብዙዎቻችን መንፈሳዊ ዓለም የማይነካና የማይጨበጥ ይመስለናል ልንረዳ የሚገባው ነገር ግን መንፈሳዊው ዓለም ከስጋዊው ዓለም በላይ እውነተኛና የበለጠ ተጨባች መሆኑን ነው።

ንፋስ ስላላየነው የለም እንደማንለው ሁሉ መንፈሳዊውን ዓለም ስላላየነው የለም ማለት አንችልም ምክንያቱም ሳናየው ተፅዕኖውን ስለምናየው ነዉ።

እግዚአብሔር የሚነካ ነገር ሆኖ ከመንፈሳዊ ዓለም የሰጠን ትልቁ መሳሪያ መፅሐፍ ቅዱስ ነው።

“ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤”
— ያዕቆብ 1፥23

#ቃሉ_ለመንፈሳዊው_ዓለም_መስታወት_ነው_!

ብዙዎቻችን መንፈሳዊው ዓለም ምን እንደሆነ እንገምታለን እግዚአብሔር ግን እንዳንገምት በመጽሐፍ ጽፎ አስቀምጦልናል።

ስለዚህ ክርስቲያን በግዑዙ ዓለም የሚኖረው ሕይወት የሚወሰነው መንፈሳዊውን አለም ባወቀውና በተረዳው ልክ ነው።

ለዚህ ነው ክርስቲያን ለቃሉ ጊዜና ዋጋ ሊሰጥ የሚገባው ምክንያቱም ቃሉ ምርኮአችንን እና ርስታችንን ይሰጠናል።

“ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።”
— መዝሙር 119፥162

ብዙ ሰዎች ስኬት ከስራ ቦታ የሚጀምር ይመስላቸዋል ነገር ግን ስኬት የሚጀምረው ከስጋዊ ዓለም ሳይሆን ከመንፈሳዊው ዓለም ነው!

መልካም ቀን


https://t.me/One_way_He